Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የገ​ሊላ ክፍል በም​ት​ሆን በቃና ሰርግ ሆነ፤ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ እና​ትም በዚያ ነበ​ረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በሦስተኛው ቀን፣ በገሊላ አውራጃ፣ በቃና ከተማ ሰርግ ነበር፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በሦስተኛው ቀን፥ በገሊላ ምድር በምትገኘው ቃና በምትባል ከተማ ሠርግ ነበረ፤ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 2:1
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።


አባቶች ለልጆቻቸው ቤትንና ሀብትን ያወርሳሉ፤ ሚስት ግን በእግዚአብሔር ከባልዋ ጋር አንድ ትሆናለች።


ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ደግሞ ዮሐ​ንስ ከሁ​ለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ቆሞ ሳለ፥


እር​ሱም ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ወሰ​ደው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ባየው ጊዜ፥ “ አንተ የዮና ልጅ ስም​ዖን ነህን? አንተ ኬፋ ትባ​ላ​ለህ፤” አለው፤ ትር​ጓ​ሜ​ውም ጴጥ​ሮስ ማለት ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮስ፥ ዲዲ​ሞስ የሚ​ሉት ቶማስ፥ ከገ​ሊላ ቃና የሆ​ነው ናት​ና​ኤል፥ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆ​ችና ሌሎ​ችም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለት አብ​ረው ነበሩ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ውኃ​ውን የወ​ይን ጠጅ ወደ አደ​ረ​ገ​በት የገ​ሊላ ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ቃና ዳግ​መኛ ሄደ። በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ልጁ የታ​መ​መ​በት የን​ጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤


መጋ​ባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ርኵ​ሰት የለ​ውም፤ ሴሰ​ኞ​ች​ንና አመ​ን​ዝ​ሮ​ችን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል።


ከዚ​ያም ወደ ኤብ​ሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ አሜ​ማ​ህን፥ ወደ ቀን​ታን እስከ ታላቁ ሲዶና ይደ​ር​ሳል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች