Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 12:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ሕዝ​ቡም፥ “እኛስ ክር​ስ​ቶስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ኖር በኦ​ሪት ሰም​ተን ነበር፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አንተ ‘የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ አለው’ ትለ​ና​ለህ? እን​ግ​ዲህ ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለ​ሱ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ሕዝቡም፣ “እኛስ ክርስቶስ ለዘላለም እንደሚኖር ከሕግ ሰምተናል፤ ታዲያ፣ ‘የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ማለት አለበት’ እንዴት ትላለህ? ይህስ ‘የሰው ልጅ’ ማን ነው?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 እንዲህ ሕዝቡ “እኛስ ክርስቶስ ለዘለዓለም እንዲኖር ከሕጉ ሰምተናል፤ አንተስ የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ እንዲያስፈልገው እንዴት ትላላህ? ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ሰዎቹም “በሕግ ተጽፎ የምናገኘው ‘መሲሕ ለዘለዓለም ይኖራል’ የሚል ነው፤ ታዲያ፥ አንተ፥ ‘የሰው ልጅ ወደ ላይ ከፍ ማለት አለበት’ እንዴት ትላለህ? ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እንዲህ ሕዝቡ፦ “እኛስ ክርስቶስ ለዘላለም እንዲኖር ከሕጉ ሰምተናል አንተስ የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ እንዲያስፈልገው እንዴት ትላላህ? ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 12:34
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል፤ ዙፋ​ኑን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።


ለጌ​ት​ነቱ መታ​ሰ​ቢ​ያን አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው።


መቅን ከቅ​ል​ጥም እን​ደ​ሚ​ወጣ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይወ​ጣል። ልባ​ቸ​ውም ከት​ዕ​ቢት አለፈ።


በው​ር​ደቱ ፍርዱ ተወ​ገደ፤ ሕይ​ወቱ ከም​ድር ተወ​ግ​ዷ​ልና ልደ​ቱን ማን ይና​ገ​ራል? ስለ ሕዝቤ ኀጢ​አት ለሞት ደረሰ።


ለአ​ለ​ቆች ሰላ​ምን ለእ​ር​ሱም ሕይ​ወ​ትን አመ​ጣ​ለ​ሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ በፍ​ር​ድና በጽ​ድቅ ያጸ​ና​ውና ይደ​ግ​ፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆ​ናል፤ በዳ​ዊት ዙፋን መን​ግ​ሥቱ ትጸ​ና​ለች፤ ለሰ​ላ​ሙም ፍጻሜ የለ​ውም። የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ይህን ያደ​ር​ጋል።


አንካሳይቱንም ለቅሬታ፥ ወደ ሩቅም የተጣለችውን ለብርቱ ሕዝብ አደርጋታለሁ፥ ከዚያም ወዲያ እስከ ዘላለም ድረስ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በእነርሱ ላይ ይነግሣል።


ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” ብሎ ጠየቀ።


ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ “ይህ ማን ነው?” ብሎ ተናወጠ።


ኢየሱስም “ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፤” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አማ​ል​ክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በኦ​ሪ​ታ​ችሁ ተጽፎ የለ​ምን?


እኔም ከም​ድር ከፍ ከፍ ካልሁ ሁሉን ወደ እኔ እስ​ባ​ለሁ።”


ነገር ግን በኦ​ሪ​ታ​ቸው፦ በከ​ንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሰ​ውን ልጅ ከፍ ከፍ በአ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ አባቴ እንደ አስ​ተ​ማ​ረ​ኝም እን​ዲሁ እና​ገ​ራ​ለሁ እንጂ የም​ና​ገ​ረው ከእኔ አይ​ደ​ለም።


አን​ደ​በት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለ​ምም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በኦ​ሪት ላሉት እንደ ተነ​ገረ እና​ው​ቃ​ለን።


እን​ግ​ዲህ በአ​ንዱ ሰው በደል ዓለም ሁሉ እንደ ተፈ​ረ​ደ​በት፥ እን​ዲሁ ደግሞ በአ​ንዱ ሰው ጽድቅ ሰው ሁሉ ይጸ​ድ​ቃል።


እርሱ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤ ክህ​ነቱ አይ​ሻ​ር​ምና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች