Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 11:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አት መጥ​ተው በቤት ከእ​ር​ስዋ ጋር የነ​በሩ አይ​ሁ​ድም ፈጥና ተነ​ሥታ እንደ ወጣች ባዩ ጊዜ በዚያ ለወ​ን​ድ​ምዋ ልታ​ለ​ቅስ ወደ መቃ​ብሩ የም​ት​ሄድ መስ​ሎ​አ​ቸው ተከ​ተ​ሉ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ማርያምን ሲያጽናኑ በቤት ውስጥ የነበሩ አይሁድም፣ ብድግ ብላ መውጣቷን ሲያዩ፣ ወደ መቃብሩ ሄዳ የምታለቅስ መስሏቸው ተከተሏት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ከእርሷ ጋር በቤት ሲያጽናኑአት የነበሩ አይሁድም፥ ማርያም ፈጥና እንደ ተነሣችና እንደ ወጣች ባዩ ጊዜ፥ ወደ መቃብር ሄዳ በዚያ ልታለቅስ መስሎአቸው ተከተሉአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እርስዋን ለማጽናናት መጥተው በቤት ውስጥ አብረዋት የነበሩ አይሁድ ማርያም በፍጥነት ተነሥታ ስትወጣ አይተው ወደ አልዓዛር መቃብር ሄዳ የምታለቅስ መስሎአቸው ተከተሉአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ሲያጽናኑአት ከእርስዋ ጋር በቤት የነበሩ አይሁድም ማርያም ፈጥና እንደ ተነሣችና እንደ ወጣች ባዩ ጊዜ፥ ወደ መቃብር ሄዳ በዚያ ልታለቅስ መስሎአቸው ተከተሉአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 11:31
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ።


ከአ​ይ​ሁ​ድም ስለ ወን​ድ​ማ​ቸው ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አ​ቸው ወደ ማር​ያ​ምና ወደ ማርታ የሄዱ ብዙ​ዎች ነበሩ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እር​ስዋ ስታ​ለ​ቅስ፥ ከእ​ር​ስዋ ጋር የመጡ አይ​ሁ​ድም ሲያ​ለ​ቅሱ ባየ ጊዜ በልቡ አዘነ፤ በራ​ሱም ታወከ።


መን​ፈስ ቅዱስ ያደ​ረ​በት ሰው ግን ሁሉን ይመ​ረ​ም​ራል፤ እር​ሱን ግን የሚ​መ​ረ​ም​ረው የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች