Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ማር​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኖረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ማርታም ኢየሱስን እንዲህ አለችው፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተ በዚህ ብትሆን ኖሮ፣ ወንድሜ ባልሞተ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ማርታም ኢየሱስን “ጌታ ሆይ! አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ማርታ ኢየሱስን፥ “ጌታ ሆይ! አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ፥ ወንድሜ ባልሞተም ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ማርታም ኢየሱስን፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 11:21
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ስ​ዋም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? አን​ተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ታሳ​ስብ ዘንድ፥ ልጄ​ንስ ትገ​ድል ዘንድ ወደ እኔ መጥ​ተ​ሃ​ልን?” አለ​ችው።


ይህንም ሲነግራቸው አንድ መኰንን መጥቶ “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፤” እያለ ሰገደለት።


ማር​ያም ግን ጌታ​ች​ንን ሽቱ የቀ​ባ​ችው፥ እግ​ሩ​ንም በጠ​ጕ​ርዋ ያሸ​ችው ናት፤ ወን​ድ​ምዋ አል​ዓ​ዛ​ርም ታሞ ነበር።


እኅ​ቶ​ቹም፥ “ጌታ​ችን ሆይ፥ እነሆ፥ የም​ት​ወ​ደው ታሞ​አል” ብለው ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ላኩ።


ማር​ያ​ምም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ አለ​በት ስፍራ ደረ​ሰ​ችና በአ​የ​ችው ጊዜ ከእ​ግሩ በታች ሰግዳ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኑረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር” አለ​ችው።


ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል፥ “ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ዐይን ያበ​ራው ይህ ሰው ይህስ እን​ዳ​ይ​ሞት ሊያ​ደ​ርግ ባል​ቻ​ለም ነበ​ርን?” ያሉ ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች