Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 1:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ዮሐ​ን​ስም ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ከሰ​ማይ እንደ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀ​መጥ አየሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከዚያም ዮሐንስ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ሰጠ፤ “መንፈስ እንደ ርግብ ከሰማይ ወርዶ በርሱ ላይ ሲያርፍ አየሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ “መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይም ሲኖር አየሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ቀጥሎም ዮሐንስ እንዲህ ሲል መሰከረ፦ “መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ ከሰማይ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍበት አየሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ፦ መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 1:32
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ፥ የጥ​በ​ብና የማ​ስ​ተ​ዋል መን​ፈስ፥ የም​ክ​ርና የኀ​ይል መን​ፈስ፥ የዕ​ው​ቀ​ትና የእ​ው​ነት መን​ፈስ ያር​ፍ​በ​ታል።


ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኀ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤


ወዲያውም ከውሃው በወጣ ጊዜ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርድበት አየና “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፤


መን​ፈስ ቅዱ​ስም የር​ግብ መልክ ባለው አካል አም​ሳል በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ ከሰ​ማ​ይም፥ “የም​ወ​ድህ፥ በአ​ን​ተም ደስ የሚ​ለኝ ልጄ አንተ ነህ” የሚል ቃል መጣ። ሉቃ. 9፥35።


እኔ አላ​ው​ቀ​ውም ነበር፤ ነገር ግን እስ​ራ​ኤል እን​ዲ​ያ​ው​ቁት ስለ​ዚህ እኔ በውኃ ላጠ​ምቅ መጣሁ።”


እር​ሱም ሁሉ በእ​ርሱ በኩል እን​ዲ​ያ​ምን ስለ ብር​ሃን ይመ​ሰ​ክር ዘንድ ለም​ስ​ክ​ር​ነት መጣ።


ነገር ግን ለእኔ የሚ​መ​ሰ​ክር ሌላ ነው፤ ስለ እኔ የመ​ሰ​ከ​ረው ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት እን​ደ​ሆነ አው​ቃ​ለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች