Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በሀ​ገ​ራ​ቸው ንጹ​ሑን ደም አፍ​ስ​ሰ​ዋ​ልና በይ​ሁዳ ልጆች ላይ ስለ አደ​ረ​ጉት ግፍ ግብፅ ምድረ በዳ፥ ኤዶ​ም​ያ​ስም በረሃ ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ግብጽ ባድማ፣ ኤዶምም ምድረ በዳ ትሆናለች፤ በምድራቸው ንጹሕ ደም በማፍሰስ፣ በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጽመዋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በአገራቸው ንጹሑን ደም አፍስሰዋልና በይሁዳ ልጆች ላይ ስላደረጉት ግፍ ግብጽ ምድረ በዳ፥ ኤዶምያስም በረሃ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “የግብጽና የኤዶም ሰዎች በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ስለ ፈጸሙና ንጹሑንም ሕዝብ ስለ ገደሉ፥ ‘ግብጽ ወደ በረሓነት ትለወጣለች፤ ኤዶምም ሰው የማይኖርባት ምድረ በዳ ትሆናለች።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በአገራቸው ንጹሑን ደም አፍስሰዋልና በይሁዳ ልጆች ላይ ስላደረጉት ግፍ ግብጽ ምድረ በዳ፥ ኤዶምያስም በረሃ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 3:19
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ከራ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድ​ነ​ኛ​ለህ፤ በጠ​ላ​ቶች ቍጣ ላይ እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፥ ቀኝ​ህም ያድ​ነ​ኛል


በባ​ሕ​ርም በኩል በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መር​ከ​ቦች ላይ እየ​በ​ረሩ ይወ​ር​ዳሉ፤ የም​ሥ​ራቅ ሰዎ​ች​ንና ኤዶ​ም​ያ​ስን በአ​ን​ድ​ነት ይዘ​ር​ፋሉ፤ በሞ​ዓብ ላይ ቀድ​መው እጃ​ቸ​ውን ይዘ​ረ​ጋሉ፤ የአ​ሞ​ንም ልጆች ቀድ​መው ለእ​ነ​ርሱ ይታ​ዘ​ዛሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የግ​ብ​ፅን ባሕር ያደ​ር​ቃል፤ በኀ​ይ​ለ​ኛም ነፋስ እጁን በወ​ንዙ ላይ ያነ​ሣል፤ ሰባት ፈሳ​ሾ​ች​ንም ይመ​ታል፤ ሰዎ​ችም በጫ​ማ​ቸው እን​ዲ​ሻ​ገሩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።


“ኤዶ​ም​ያ​ስም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ያ​ል​ፍ​ባ​ትም ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ ስለ መጣ​ባ​ትም መቅ​ሠ​ፍት ሁሉ ያፍ​ዋ​ጭ​ባ​ታል።


በጽ​ዮን የም​ት​ኖር በእኔ ላይ የተ​ደ​ረገ ግፍና ሥቃይ በባ​ቢ​ሎን ላይ ይሁን ትላ​ለች፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደሜ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ ይሁን ትላ​ለች።”


ሣን። በዖፅ ምድር የም​ት​ኖሪ የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዋ ደግሞ ወደ አንቺ ያል​ፋ​ልና፥ አን​ቺም ትሰ​ክ​ሪ​አ​ለሽ፥ ትራ​ቆ​ቻ​ለ​ሽም።


የአ​ብ​ድዩ ራእይ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ኤዶ​ም​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ ከባ​ቢን ወደ አሕ​ዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላ​ይ​ዋም እን​ነ​ሣና እን​ው​ጋት።


የሰውንም ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ይከድንሃል፣ የአራዊትም አደጋ ያስፈራራሃል።


ከግብጽም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፣ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ፥ የሚበቃም ቦታ አይገኝላቸውም።


ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች