Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በፍ​ርድ ሸለቆ ቀር​ቦ​አ​ልና ውካ​ታ​ዎች በፍ​ርድ ሸለቆ ተሰሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ብዙ ሕዝብ፣ በጣም ብዙ ሕዝብ፣ ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ ተሰብስቧል፤ ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ፣ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የጌታ ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቧልና የብዙ ብዙ ሕዝብ ውካታ በፍርድ ሸለቆ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ጌታ በፍርድ ሸለቆ ፍርድ የሚሰጥበት ቀን ደርሶአል፤ ስለዚህ ቊጥሩ እጅግ የበዛ ሕዝብ በዚያ ተሰብስቦአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቦአልና የብዙ ብዙ ሕዝብ ውካታ በፍርድ ሸለቆ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 3:14
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ ግን እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ደን​ቆሮ፥ አፉ​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ከ​ፍት ዲዳ ሆንሁ።


በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ። የተ​ሰ​በ​ሰቡ ነገ​ሥ​ታ​ትና የአ​ሕ​ዛብ ድም​ፅም አለ። የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተዋ​ጊ​ዎች አሕ​ዛብ ይመጡ ዘንድ አዘዘ።


ስለ ጽዮን ሸለቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ ዛሬ ወደ ሰገ​ነት በከ​ንቱ መው​ጣ​ታ​ችሁ ምን ሆና​ች​ኋል?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና ለቀኑ ወዮ! ወዮ! እር​ሱም በጥ​ፋት ላይ እንደ ጥፋት ይመ​ጣል።


በጽ​ዮን መለ​ከ​ትን ንፉ፤ በቅ​ዱ​ሱም ተራ​ራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይደ​ን​ግጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን መጥ​ቶ​አ​ልና፥ እር​ሱም ቀር​ቦ​አ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ድም​ፁን ይሰ​ጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃ​ሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን ታላ​ቅና እጅግ የም​ታ​ስ​ፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገ​ለ​ጣ​ለች፥ መጠኗ ምን​ድን ነው? ማንስ ይች​ላ​ታል?


“አሕ​ዛብ ሁሉ ይነሡ፤ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ሸለ​ቆም ይውጡ፤ በዙ​ሪያ ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ እፈ​ርድ ዘንድ በዚያ እቀ​መ​ጣ​ለ​ሁና።


አሕ​ዛ​ብን ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ሸለቆ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በተ​በ​ተ​ኑ​በ​ትና ምድ​ሬን በተ​ካ​ፈ​ሉ​በት በዚያ ስለ ወገ​ኖች ስለ ርስቴ ስለ እስ​ራ​ኤል እወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፣ የእግዚአብሔር ቀን ድምፅ ቀርቦአል እጅግም ፈጥኖአል፣ ኃያሉም በዚያ በመራራ ልቅሶ ይጮኻል።


ከው​ሾች ተጠ​በቁ፤ ከክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችም ተጠ​በቁ፤ ሥጋ​ቸ​ውን ብቻ በመ​ቍ​ረጥ ተገ​ዝ​ረ​ናል ከሚ​ሉም ተጠ​በቁ።


አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች