Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እና​ንተ የም​ድር እን​ስ​ሶች ሆይ! የም​ድረ በዳው ማሰ​ማ​ርያ ለም​ል​ሞ​አ​ልና፥ ዛፉም ፍሬ​ውን አፍ​ር​ቶ​አ​ልና፥ በለ​ሱና ወይ​ኑም ኀይ​ላ​ቸ​ውን ሰጥ​ተ​ዋ​ልና አት​ፍሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የዱር እንስሳት ሆይ፤ አትፍሩ፤ መሰማሪያ መስኮቹ ለምልመዋልና፤ ዛፎቹ ፍሬአቸውን አፍርተዋል፤ የበለሱ ዛፍና የወይኑ ተክልም እጅግ አፍርተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድረ በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኃይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እናንተም የምድር እንስሶች አትፍሩ፤ የምትሰማሩባቸው መስኮች ለምልመዋል፤ ዛፎችም አፍርተዋል፤ የበለሱና የወይኑ ፍሬ እጅግ የበዛ ሆኖአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድረ በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኃይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 2:22
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምድ​ር​ንም ባረ​ስህ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ኀይ​ል​ዋን አት​ሰ​ጥ​ህም፤ በም​ድር ላይ ኮብ​ላ​ይና ተቅ​በ​ዝ​ባዥ ትሆ​ና​ለህ።”


ጽድ​ቅ​ህን እንደ ብር​ሃን፥ ፍር​ድ​ህ​ንም እንደ ቀትር ያመ​ጣ​ታል።


በራ​ሳ​ችን ላይ ሰውን አስ​ጫ​ንህ፤ በእ​ሳ​ትና በውኃ መካ​ከል አሳ​ለ​ፍ​ኸን፥ ወደ ዕረ​ፍ​ትም አወ​ጣ​ኸን።


መባ​ዬን ይዤ ወደ ቤትህ እገ​ባ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቸ​ኞ​ችን በቤቱ ያሳ​ድ​ራ​ቸ​ዋል፥ እስ​ረ​ኞ​ች​ንም በኀ​ይሉ ያወ​ጣ​ቸ​ዋል፤ በመ​ቃ​ብር የሚ​ኖሩ ኀዘ​ን​ተ​ኞ​ች​ንም እን​ዲሁ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ደስ አሰ​ኝ​ሻ​ለሁ፤ ባድ​ማ​ሽ​ንም ሁሉ ደስ አሰ​ኛ​ለሁ፤ ምድረ በዳ​ሽ​ንም እንደ ዔድን፥ በረ​ሃ​ዎ​ች​ሽ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት አደ​ር​ጋ​ለሁ። ደስ​ታና ተድላ እም​ነ​ትና የዝ​ማሬ ድምፅ በው​ስጧ ይገ​ኝ​ባ​ታል።


ደግ​ሞም የራ​ብን ስድብ ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እን​ዳ​ት​ሸ​ከሙ የዛ​ፍን ፍሬና የእ​ር​ሻ​ውን መከር አበ​ዛ​ለሁ።


ሰዎ​ችም ባድማ የነ​በ​ረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆና​ለች፤ የፈ​ረ​ሱት፥ ባድማ የሆ​ኑት፥ የጠ​ፉ​ትም ከተ​ሞች ተመ​ሽ​ገ​ዋል፤ ሰውም የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ሆነ​ዋል ይላሉ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! ሕዝቤ ይመጡ ዘንድ ተስፋ ያደ​ር​ጋ​ሉና ወይ​ና​ች​ሁ​ንና ፍሬ​ያ​ች​ሁን ይበ​ላሉ።


እኔስ ቀኛ​ቸ​ው​ንና ግራ​ቸ​ውን የማ​ይ​ለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚ​በ​ልጡ ሰዎ​ችና ብዙ እን​ስ​ሶች ላሉ​ባት ለታ​ላ​ቂቱ ከተማ ለነ​ነዌ አላ​ዝ​ን​ምን?” አለው።


በዚያን ዘመን ሁሉ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው አሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፣ አምሳ ማድጋም ይቀዳ ዘንድ ወደ መጥመቂያው በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው ሀያ ብቻ ነው።


ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፣ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፣ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።


አሁ​ንም የሚ​ተ​ክ​ልም ቢሆን፥ የሚ​ያ​ጠ​ጣም ቢሆን የሚ​ጠ​ቅ​መው ነገር የለም፤ የሚ​ያ​ሳ​ድግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች