Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይህን ሕዝብ መከ​ራን አበ​ላ​ዋ​ለሁ፤ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጣ​ዋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ይህን ሕዝብ መራራ ምግብ አበላዋለሁ፤ የተመረዘንም ውሃ አጠጣዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የማደርገውን ነገር ልንገራችሁ፤ ይህ ሕዝብ ምግቡ መራራ መጠጡም የተመረዘ ውሃ እንዲሆንበት አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 9:15
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጠ​ላት ፊት ጽኑ ግንብ ነህ፤ ተስ​ፋ​ዬም ሆነ​ኽ​ል​ኛ​ልና መራ​ኸኝ።


ፍር​ድን ከሰ​ማይ ታሰ​ማ​ለህ። ምድር ፈራች፥ ዝምም አለች፥


ወደ ግብፅ ሀገር በሄደ ጊዜ ለዮ​ሴፍ ምስ​ክ​ርን አቆመ። የማ​ያ​ው​ቀ​ውን ቋንቋ ሰማ።


ሰውም ሁሉ ይዋ​ረ​ዳል፤ የሰ​ውም ኵራት ይወ​ድ​ቃል፤ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።


እስ​ት​ን​ፋሱ በአ​ፍ​ን​ጫው ያለ​በ​ትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈ​ጠ​ራል?


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነቢ​ያት ዘንድ ርኵ​ሰት በም​ድር ሁሉ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና ሕማ​ምን አበ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መራራ ውኃ​ንም አጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ራ​ቸ​ውና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰይ​ፍ​ንና ራብን ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ዳ​ለሁ።”


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፥ “ያል​ተ​በ​ረዘ የዚ​ህን ቍጣ የወ​ይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ አን​ተን የም​ሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ አጠ​ጣ​ቸው።


እነሆ ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክ​ፋት እተ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ያሉት የይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ ያል​ቃሉ።


በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ውን በሚ​ሹ​አት ፊት ኤላ​ምን አስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ለሁ። ክፉ ነገ​ርን እር​ሱም ጽኑ ቍጣ​ዬን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እስ​ካ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ በኋ​ላ​ቸው ሰይ​ፍን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


“ዝም ብለን ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ በደ​ልን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ፍ​ቶ​ና​ልና፥ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጥ​ቶ​ና​ልና ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ወደ ተመ​ሸጉ ከተ​ሞች እን​ግባ በዚ​ያም እን​ጥፋ።


ምሬ​ትን አጠ​ገ​በኝ፤ በሐ​ሞ​ትም አሰ​ከ​ረኝ።


ዛይ። ስደ​ቴ​ንና ችግ​ሬን፥ እሬ​ት​ንና ሐሞ​ትን አስብ።


ከአ​ን​ቺም ሢሶው በቸ​ነ​ፈር ይሞ​ታል፤ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በራብ ያል​ቃል፤ ሢሶ​ውም በዙ​ሪ​ያሽ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋ​ሳት ሁሉ እበ​ት​ና​ለሁ፤ በኋ​ላ​ቸ​ውም ሰይ​ፍን እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


የእ​ስ​ራ​ት​ህም ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ሢሶ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወስ​ደህ ዙሪ​ያ​ውን በጎ​ራዴ ትመ​ታ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋስ ትበ​ት​ና​ለህ፤ እኔም በኋ​ላ​ቸው ጎራዴ እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን፥ በአ​ን​ተም ላይ የም​ት​ሾ​ማ​ቸ​ውን አለ​ቆ​ች​ህን አን​ተና አባ​ቶ​ችህ ወዳ​ላ​ወ​ቃ​ች​ኋ​ቸው ሕዝብ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ በዚ​ያም ሌሎ​ችን የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ አማ​ል​ክ​ትን ታመ​ል​ካ​ለህ።


ሄዶ የእ​ነ​ዚ​ያን አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ያመ​ልክ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡን ዛሬ የሚ​ያ​ስት ወንድ ወይም ሴት ወይም ወገን ወይም ነገድ አይ​ኑ​ር​ባ​ችሁ፤ ሐሞ​ትና እሬ​ትም የሚ​ያ​በ​ቅል ሥር አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ።


የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል፤ የውሃውም ሲሶ መራራ ሆነ፤ መራራም ስለተደረገ በውሃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች