Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 52:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ዛ​ዦቹ አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከአ​ይ​ሁድ ሰባት መቶ አርባ አም​ስት ነፍስ ማር​ኮ​አል፤ ሰዎ​ችም ሁሉ አራት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ናቡከደነፆር በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት፣ የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ ሰባት መቶ አርባ ዐምስት አይሁድ ማርኮ ወስዷል። በአጠቃላይ አራት ሺሕ ስድስት መቶ ሰዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ሰው ማርኮ አፈለሰ፤ በአጠቃላይ የሰዎቹ ብዛት አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እንዲሁም በነገሠ በሃያ ሦስት ዓመቱ ሰባት መቶ አርባ አምስት አይሁድ በናቡዛርዳን እጅ ተማርከው ተወስደዋል፤ በጠቅላላው ተማርከው የተወሰዱት ሰዎች ቊጥር አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ነፍስ ማርኮአል፥ ሰዎች ሁሉ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 52:30
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወሰደ።


በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዐ​ሥራ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት የሚ​ቆ​መው የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ።


የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ ኰብ​ል​ለ​ውም ወደ እርሱ የገ​ቡ​ትን ሰዎ​ችና የቀ​ረ​ው​ንም የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው።


የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን የሕ​ዝ​ቡን ድኆች፥ በከ​ተ​ማም ውስጥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ፥ ሸሽ​ተ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ የተ​ጠ​ጉ​ትን፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ቅሬታ አመጣ።


ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ስም​ንት መቶ ሠላሳ ሁለት ነፍስ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ማር​ኮ​አል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰው ወይ​ንን እን​ደ​ሚ​ቃ​ርም፥ እን​ዲሁ ከእ​ስ​ራ​ኤል የቀ​ሩ​ትን ይቃ​ር​ሙ​አ​ቸ​ዋል፤ እጅ​ህን እንደ ወይን ለቃሚ ወደ እን​ቅብ ዘርጋ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች