Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 52:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የና​ሱም ጕል​ላት በላዩ ነበረ፤ የአ​ን​ዱም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በጕ​ል​ላ​ቱም ላይ በዙ​ሪ​ያው ሁሉ ከናስ የተ​ሠሩ መር​በ​ብና ሮማ​ኖች ነበ​ሩ​በት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዐምድ ደግሞ እን​ደ​ዚህ ያለ ነገ​ርና ሮማ​ኖች ነበ​ሩ​በት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በአንዱ ዐምድ ዐናት ላይ ያለው የናስ ጕልላት ቁመት ዐምስት ክንድ ሲሆን፣ ዙሪያውንም ሁሉ የሮማን ቅርጽ ባላቸው የናስ ጌጣጌጦች የተዋበ ነበር፤ ሌላውም ዐምድ የሮማኑን ጌጣጌጥ ጨምሮ ከዚሁ ጋራ ተመሳሳይ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የናሱም ጉልላት በላዩ ነበረ፤ የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፥ በጉልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት፤ በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የእያንዳንዱም ምሰሶ ጒልላት ከነሐስ የተሠራ ሆኖ ሁለት ሜትር ያኽል ከፍታ የነበረውና በመረብና በሮማን ፍሬ ቅርጽ የተጌጠ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የናሱም ጕልላት በላዩ ነበረ፥ የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፥ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት፥ በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 52:22
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ በነ​በ​ሩት ጕል​ላ​ቶች ላይ በመ​ር​በቡ ሥራ አጠ​ገብ ሮማ​ኖ​ቹን አደ​ረገ። ሮማ​ኖ​ቹም በአ​ንዱ ወገን ሁለት መቶ ነበሩ። የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ጕል​ላት እን​ዲሁ ነበረ።


በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች ይሸ​ፍኑ ዘንድ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መር​በብ በሁ​ለት በሁ​ለት ተራ አድ​ርጎ ለሁ​ለቱ መር​በ​ቦች አራት መቶ ሮማ​ኖ​ችን አደ​ረገ።


የአ​ን​ዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስም​ንት ክንድ ነበረ፥ የና​ስም ጕል​ላት ነበ​ረ​በት፤ የጕ​ል​ላ​ቱም ርዝ​መት ሦስት ክንድ ነበረ፥ በጕ​ል​ላ​ቱም ላይ በዙ​ሪ​ያው የናስ መር​በ​ብና ሮማ​ኖች ነበሩ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓምድ ላይ መር​በብ ነበ​ረ​በት።


በቤ​ቱም ፊት ቁመ​ታ​ቸው ሠላሳ አም​ስት ክንድ የነ​በ​ረ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች ሠራ፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም ላይ የነ​በ​ረው ጕል​ላት አም​ስት ክንድ ነበረ።


የሁ​ለ​ቱ​ንም ቋዶች ጫፎች በሁ​ለቱ ፈር​ጦች ውስጥ አግ​ብ​ተህ በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ በስ​ተ​ፊት በመ​ጋ​ጠ​ሚ​ያ​ቸው ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች