Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 51:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ይነ​ግር ዘንድ ሯጩ ሯጩን ለመ​ገ​ና​ኘት፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውን ለመ​ገ​ና​ኘት ይሮ​ጣል፤ ከተ​ማዋ ከዳር እስከ ዳር ተይ​ዛ​ለ​ችና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከተማዪቱ ሙሉ በሙሉ መያዟን፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር፣ አንዱ ወሬኛ ሌላውን ወሬኛ፣ አንዱ መልእክተኛ ሌላውን መልእክተኛ ወዲያው ወዲያው ይከተላል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንደኛው ሯጭ ሌላውን ሯጭ አንዱም መልእክተኛ ሌላውን መልእክተኛ ለመገናኘት ይሮጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 የእርሱ ከተማ ከዳር እስከ ዳር የተያዘች መሆንዋን ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንዱ ሩዋጭ ለሌላው ሩዋጭ፥ አንዱ መልእክተኛ ለሌላው መልእክተኛ መልእክቱን ለማስተላለፍ ይሯሯጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31-32 ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች መልካዎችዋም እንደ ተያዙ፥ ቅጥርዋም በእሳት እንደ ተቃጠለ፥ ሰልፈኞችም እንደ ደነገጡ ለባቢሎን ንጉሥ ይነግር ዘንድ ወሬኛው ወሬኛውን መልእክተኛውም መልእክተኛውን ሊገናኝ ይሮጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 51:31
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ ንጉ​ሡም ትእ​ዛዝ መል​እ​ክ​ተ​ኞቹ እን​ዲህ የሚ​ለ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ደብ​ዳቤ ይዘው ወደ እስ​ራ​ኤ​ልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ፈጥ​ነው ሄዱ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ ወዳ​መ​ለጠ ቅሬ​ታ​ችሁ እን​ዲ​መ​ለስ ወደ አብ​ር​ሃ​ምና ወደ ይስ​ሐቅ ወደ ያዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለሱ።


ሕይ​ወቴ ከሚ​ሮጥ ሰው ይልቅ ይፈ​ጥ​ናል፤ ይሸ​ሻል፥ መል​ካ​ም​ንም አያ​ይም።


መከራ በመ​ከራ ላይ ተጠ​ር​ቶ​አል፤ ምድር ሁሉ ተዋ​ር​ዳ​ለ​ችና፤ በድ​ን​ገ​ትም ድን​ኳኔ ጠፋ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም ተቀ​ዳ​ደዱ።


“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥ አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤ በሉ።


ባቢ​ሎን ሆይ! በመ​ከ​ራው ተይ​ዘሽ ጠፋሽ፤ አን​ቺም ይህ እን​ደ​መ​ጣ​ብሽ አላ​ወ​ቅ​ሽም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​መ​ሽ​ዋ​ልና ተገ​ኝ​ተ​ሻል፤ ተይ​ዘ​ሽ​ማል።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ውካ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ቶ​አል፤ እጁም ደክ​ማ​ለች፤ ምጥ ወላድ ሴትን እን​ደ​ሚ​ይ​ዛ​ትም ጭን​ቀት ይዞ​ታል፤


መሻ​ገ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተይ​ዘ​ዋ​ልና፥ ቅጥ​ር​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ሎ​አ​ልና፥ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ተማ​ር​ከ​ዋ​ልና።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች