ኤርምያስ 49:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ማን ይመጣብኛል ብለሽ በሀብትሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! በጠፉ ሸለቆዎችሽ ስለ ምን ትመኪያለሽ? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤ በሸለቆችሽ ለምን ትመኪያለሽ? ለምንስ በፍሬያማ ሸለቆሽ ትኵራሪያለሽ? በብልጽግናሽ ተማምነሽ፣ ‘ማን ሊነካኝ ይችላል?’ ትያለሽ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ማን በእኔ ላይ ይመጣብኛል ብለሽ በመዝገብሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! በሸለቆችሽ፥ ውኃ በሚፈስስባቸው ሸለቆችሽ፥ ለምን ትመኪያለሽ? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እየቀነሰ በሚሄደው ኀይላችሁ የምትመኩት ለምንድን ነው? እናንተ እምነተቢስ ሕዝብ ሆይ! ‘አደጋ የሚጥልብኝ ማነው?’ ብላችሁ በሀብታችሁ ክምችት ተመክታችኋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ማን ይመጣብኛል ብለሽ በመዝገብሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፥ በሸለቆችሽ፥ ውኃ በሚያረካቸው ሸለቆችሽ፥ ስለ ምን ትመኪያለሽ? ምዕራፉን ተመልከት |