ኤርምያስ 48:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)44 እርስዋን በምጐበኝበት ዓመት በሞአብ ላይ ይህን አመጣለሁ፤ በፍርሀት የሸሸ በጕድጓድ ውስጥ ይወድቃል፤ ከጕድጓድም የወጣ በወጥመድ ይያዛል፤ ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም44 “ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ፣ ጕድጓድ ውስጥ ይገባል፤ ከጕድጓዱም የሚወጣ፣ በወጥመድ ይያዛል፤ በሞዓብ ላይ፣ የቅጣቱን ዓመት አመጣለሁና፣” ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)44 በሞዓብ ላይ የመጐብኘትን ዓመት አመጣበታለሁና፥ ይላል ጌታ፤ ከአስፈሪውም ነገር የሸሸ በጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጉድጓድም ውስጥ የሚወጣ በወጥመድ ይያዛል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም44 “ከሽብር የሚያመልጠው፥ ጒድጓድ ውስጥ ይገባል፤ ከጒድጓድ ዘሎ የሚወጣውም ሁሉ በወጥመድ ይያዛል፤ ሞአብን የምቀጣበትን ቀን አመጣባታለሁ” ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)44 በሞዓብ ላይ የመጐብኘትን ዓመት አመጣበታለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍርሃት የሸሸ በጕድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጕድጓድም የወጣ በወጥመድ ይያዛል። ምዕራፉን ተመልከት |