Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 48:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 አንቺ የሴ​ባማ ወይን ሆይ! የኢ​ያ​ዜ​ርን ልቅሶ ለአ​ንቺ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችሽ ባሕ​ርን ተሻ​ግ​ረ​ዋል፤ ወደ ኢያ​ዜ​ርም ባሕር ደር​ሰ​ዋል፤ ሳይ​በ​ስል በሰ​ብ​ል​ሽና በወ​ይ​ንሽ ላይ ጥፋት መጥ​ቶ​አል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 የሴባማ ወይን ሆይ፤ ለኢያዜር ካለቀስሁት እንኳ ይልቅ አለቅስልሻለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ እስከ ባሕሩ ተዘርግተዋል፤ እስከ ኢያዜርም ደርሰዋል፤ ለመከር በደረሰው ፍሬሽና በወይንሽ ላይ፣ አጥፊው መጥቷል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ! ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፥ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፤ አጥፊው በበጋ ፍሬሽና በወይንሽ ላይ መጥቷል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ለያዕዜር ሕዝብ ከማለቅሰው ይበልጥ ለሲብማ ሕዝብ እየጮኽኩ አለቅሳለሁ፤ የሲብማ ከተማ ሆይ! እንቺ ቅርንጫፎችዋ ሙት ባሕርን አልፎ እስከ ያዜር እንደሚደርስ የወይን ተክል ነሽ፤ ነገር ግን በጐመራው ፍሬሽና በወይን ዘለላሽ ላይ አጥፊው መጥቷል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ፥ ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ፥ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፥ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፥ አጥፊው በሰብልሽና በወይንሽ ላይ መጥቶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 48:32
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚ​መ​ጡት ከለ​ዳ​ው​ያን ፊት እቆም ዘንድ በመ​ሴፋ እኖ​ራ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ወይ​ኑ​ንና ፍሬ​ውን፥ ዘይ​ቱ​ንም አከ​ማቹ፤ በየ​ዕ​ቃ​ች​ሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያ​ዛ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​መጡ።”


ሞዓብ ፈር​ሳ​ለች፤ ከተ​ሞ​ቹ​ዋም ጠፍ​ተ​ዋል፤ የተ​መ​ረ​ጡ​ትም ጐል​ማ​ሶ​ችዋ ወደ መታ​ረድ ወር​ደ​ዋል፥ ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በዲ​ቦን የም​ት​ኖሪ ሆይ! ሞአ​ብን የሚ​ያ​ጠፋ ወጥ​ቶ​ብ​ሻ​ልና፥ አም​ባ​ሽ​ንም ሰብ​ሮ​አ​ልና ከክ​ብ​ርሽ ውረጂ፤ በጭ​ቃም ላይ ተቀ​መጪ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ ጥፋት ወደ ከተማ ሁሉ ይመ​ጣል፤ አን​ዲ​ትም ከተማ አት​ድ​ንም፤ ሸለ​ቆ​ውም ይጠ​ፋል፤ ሜዳ​ውም ይበ​ላ​ሻል።


ሙሴም ሰላ​ዮ​ቹን ወደ ኢያ​ዜር ላከ፤ እር​ስ​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ያዙ፤ በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አባ​ረሩ።


ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች እጅግ ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ያ​ዜር ምድ​ርና የገ​ለ​ዓድ ምድር የከ​ብት ሀገር እንደ ነበረ አዩ።


“አጣ​ሮት፥ ዲቦን፥ ያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴ​ቦን፥ ኤል​ያሌ፥ ሲባማ፥ ናባው፥ ቤያን፤


ሶፋ​ንን፥ ኢያ​ዜ​ርን፥


እነ​ዚ​ህ​ንም የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች በየ​ስ​ማ​ቸው ጠሩ​አ​ቸው።


ቂር​ያ​ታ​ይም፥ ሴባማ፥ ሲራ​ዳት፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም ተራራ ያለ​ችው ሲዮን፥


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢያ​ዜ​ርና የገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ሁሉ፥ የአ​ሞ​ንም ልጆች ምድር እኩ​ሌታ በራ​ባት ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አሮ​ዔር ድረስ፥


ሐሴ​ቦ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች