Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 48:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “ሞአብ ከል​ጅ​ነቷ ጀምራ ዐረ​ፈች፤ በክ​ብ​ር​ዋም ቅም​ጥል ነበ​ረች፤ ወይ​ን​ዋም ከዕቃ ወደ ዕቃ አል​ተ​ገ​ላ​በ​ጠም፤ ወደ ምር​ኮም አል​ሄ​ደ​ችም፤ ስለ​ዚህ ቃናው በእ​ር​ስዋ ውስጥ ቀር​ቶ​አል፤ መዓ​ዛ​ዋም አል​ተ​ለ​ወ​ጠም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ሞዓብ በአንቡላው ላይ እንዳረፈ የወይን ጠጅ፣ ከልጅነት ጀምሮ የተረጋጋ ነበረ፤ ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ በምርኮም አልተወሰደም፤ ቃናው እንዳለ ነው፤ መዐዛውም አልተለወጠም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሞዓብ ከብላቴንነቱ ጀምሮ ተረጋግቷል፥ በአምቡላውም ላይ ዐርፎአል፥ ከዕቃም ወደ ዕቃ አልተንቈረቈረም፥ ወደ ምርኮም አልሄደም፤ ስለዚህ ቃናው በእርሱ ውስጥ ቀርቶአል፥ መዓዛውም አልተለወጠም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከዕቃ ወደ ዕቃ ሳይገለባበጥ ከአተላው ጋር አብሮ የቈየ የወይን ጠጅ ጣዕሙ እንዳለ ይቈያል፤ መዓዛውም አይለወጥም፤ እንደዚሁም የሞአብ ሕዝብ አገራቸው ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ሳይታወኩ ኖረዋል፤ ተማርከውም አይታወቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሞዓብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ቅምጥል ነበረ፥ በአምቡላውም ላይ ዐርፎአል፥ ከዕቃውም ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፥ ወደ ምርኮም አልሄደም፥ ስለዚህ ቃናው በእርሱ ውስጥ ቀርቶአል፥ መዓዛውም አልተለወጠም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 48:11
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በውኃ ባሰ​ጠ​ሙን ነበር ብዬ በተ​ጠ​ራ​ጠ​ርሁ ነበር፤


አላዋቂዎችን አለመመለሳቸው ትገድላቸዋለችና፥ ሰነፎችንም ምርመራቸው ትገድላቸዋለች።


የሞ​ዓ​ብን ትዕ​ቢ​ትና እጅግ መኵ​ራ​ቱን ሰም​ተ​ናል፤ ትዕ​ቢ​ቱ​ንም አስ​ወ​ገ​ድሁ፤ ጥን​ቈ​ላህ እን​ዲህ አይ​ደ​ለ​ምና፥ እን​ዲ​ህም አይ​ደ​ለም፤


እነሆ፥ ምድር መፈ​ታ​ትን ትፈ​ታ​ለች፤ ፈጽ​ማም ትበ​ረ​በ​ራ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ዲህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ግብ​ዣን ያደ​ር​ጋል፤ በዚህ ተራራ ላይ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንም ይጠ​ጣሉ፤ ዘይ​ት​ንም ይቀ​ባሉ።


በጐ​ሰ​ቈ​ልሽ ጊዜ ተና​ገ​ር​ሁሽ፤ አን​ቺም፦ አል​ሰ​ማም አልሽ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀምሮ ቃሌን አለ​መ​ስ​ማ​ትሽ መን​ገ​ድሽ ነው።


ስለ​ዚህ እነሆ ጠማ​ሞ​ችን የም​ል​ክ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ሙ​በ​ታል፤ ጋኖ​ቹ​ንም ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ ፊቀ​ኖ​ቹ​ንም ይሰ​ብ​ራሉ።


የሞ​አ​ብን ስድብ፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንም ብዙ ውር​ደ​ቱን፥ ልቡ​ና​ው​ንም ያስ​ታ​በ​የ​በ​ትን ትዕ​ቢ​ቱን ሰም​ተ​ናል።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በላኝ፤ ከፋ​ፈ​ለ​ኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደ​ረ​ገኝ፤ እንደ ዘን​ዶም ዋጠኝ፤ ከሚ​ጣ​ፍ​ጠ​ውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።


ባዶና ባድማ ምድረ በዳም ሆናለች፣ ልብ ቀልጦአል፥ ጕልበቶችም ተብረክርከዋል፣ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሰዎችም ሁሉ ፊት ጠቍሮአል።


ዘራፊዎች ዘርፈዋቸዋልና፥ የወይናቸውንም አረግ አጥፍተዋልና እግዚአብሔር የያዕቆብን ክብር እንደ እስራኤል ክብር ይመልሳል።


በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እመረምራለሁ፣ በአተላቸውም ላይ የሚቀመጡትን፥ በልባቸውም፦ እግዚአብሔር መልካምን አያደርግም፥ ክፉም አያደርግም የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።


እኔ ጥቂት ብቻ ተቈጥቼ ሳለሁ እነርሱ ክፋትን ስላገዙት፥ ባልተቸገሩት አሕዛብ ላይ እጅግ ተቈጥቻለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች