Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 47:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከኀ​ይ​ለ​ኞች ፈረ​ሶች ከኮ​ቴ​ያ​ቸው መጠ​ብ​ጠብ ድምፅ፥ ከሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹም መሽ​ከ​ር​ከር፥ ከመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም መት​መም የተ​ነሣ አባ​ቶች በእ​ጃ​ቸው ድካም ምክ​ን​ያት ወደ ልጆ​ቻ​ቸው አይ​መ​ለ​ሱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከፈረስ ኮቴ ድምፅ፣ ከጠላት ሠረገላ ጩኸትና ከሠረገላው ሽክርክሪት ፍትጊያ ድምፅ የተነሣ፣ አባቶች ልጆቻቸውን ለመርዳት ወደ ኋላ መለስ አይሉም፤ እጃቸውም ስንኩል ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከኃይለኞች ፈረሶቹ የኮቴያቸው ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መንጐድ፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ወደ ልጆቻቸው ዘወር ብለው አይመለከቱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከሚጋልቡ ፈረሶች ኮቴ ድምፅ፥ ከጠላት መንኰራኲር ድምፅ፥ ከሠረገሎቻቸው መትመም የተነሣ አባቶች ኀይላቸው በመድከሙ ምክንያት ልጆቻቸውን እንኳ ለመርዳት ወደ ኋላ አይመለሱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከኃይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መሽከርከር፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ፊታቸውን መልሰው ወደ ልጆቻቸው አይመለከቱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 47:3
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፍላ​ጾ​ቻ​ቸው ተስ​ለ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተለ​ጥ​ጠ​ዋል፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም መን​ኰ​ራ​ኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈ​ጠ​ራል።


በፈ​ረ​ሶች ተቀ​መጡ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንም አዘ​ጋ​ጁና ውጡ፤ ጋሻም የሚ​ያ​ነ​ግቡ የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያና የሊ​ብያ ኀያ​ላን፥ ቀስ​ት​ንም ይዘው የሚ​ስቡ የሉድ ኀያ​ላን ይውጡ።


ቀስ​ትና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ይተ​ም​ማል፤ በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የባ​ቢ​ሎን ሴት ልጅ ሆይ እንደ እሳት በአ​ንቺ ላይ ይሰ​ለ​ፋሉ።


የፈ​ረ​ሶ​ቹን የሩጫ ድምፅ ከዳን ሰማን፤ ከሠ​ራ​ዊቱ ፈረ​ሶች ሩጫ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ምድር በመ​ላዋ ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች፤ መጥ​ተ​ውም ምድ​ሪ​ቱ​ንና በእ​ር​ስ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ፥ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንና የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ት​ንም በሉ።


ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ሰዎች ሁሉ በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ርና በሠ​ረ​ገላ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ጉባኤ ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ ጋሻና አላ​ባሽ ጋሻ፥ ራስ ቍርም ይዘው በዙ​ሪ​ያሽ ጥበቃ ያደ​ር​ጋሉ፤ ፍር​ድ​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ፍር​ዳ​ቸ​ውም ይፈ​ር​ዱ​ብ​ሻል።


ሰረገሎች በመንገድ ላይ ይነጕዳሉ፥ አደባባይም ይጋጫሉ፣ መልካቸው እንደ ፋና ነው፥ እንደ መብረቅም ይከንፋሉ።


ነነዌ ግን ከዱሮ ዘመን ጀምራ እንደ ተከማቸ ውኃ ነበረች፣ አሁን ግን ይሸሻሉ፣ እነርሱም፦ ቁሙ፥ ቁሙ ይላሉ፥ ነገር ግን የሚመለስ የለም።


የብረት ጥሩር የሚመስልም ጥሩር ነበራቸው፤ የክንፋቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች ሰረገላዎች ድምፅ ነበረ።


ያን ጊዜ ከኀ​ያ​ላን ግል​ቢያ ብር​ታት የተ​ነሣ፥ የፈ​ረ​ሶች ጥፍ​ሮች ተቀ​ጠ​ቀጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች