Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 43:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “ታላ​ላ​ቆ​ችን ድን​ጋ​ዮች በእ​ጅህ ውሰድ፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች እያዩ በጣ​ፍ​ናስ ባለው በፈ​ር​ዖን ቤት ደጅ መግ​ቢያ ሸሽ​ጋ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ትልልቅ ድንጋዮች ውሰድና በጣፍናስ ባለው የፈርዖን ቤተ መንግሥት በር ላይ የይሁዳ ሰዎች እያዩ በሸክላ ጡብ ወለል ውስጥ ቅበራቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “ትላልቅ ድንጋዮች በእጅህ ውሰድ፥ የይሁዳም ሰዎች እያዩ በጣፍናስ በፈርዖን ቤት መግቢያ ባለው በቅጥራኑና በጡቡ ደጃፍ ሸሽጋቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “ጥቂት ታላላቅ ድንጋዮች ፈልገህ ካገኘህ በኋላ ከእስራኤል ልጆች ጥቂቱ እያዩህ በከተማይቱ ቤተ መንግሥት መግቢያ ፊት ለፊት ባለው ከሲሚንቶ በተሠራው ወለል ሥር ቅበረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ታላላቆችን ድንጋዮች በእጅህ ውሰድ፥ የይሁዳም ሰዎች እያዩ በጣፍናስ ባለው በፈርዖን ቤት ደጅ መግቢያ ሸሽጋቸው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 43:9
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ አው​ጥቶ በመ​ጋ​ዝና በብ​ረት መቈ​ፈ​ሪያ በብ​ረት መጥ​ረ​ቢ​ያም ሥር አኖ​ራ​ቸው፤ በሸ​ክላ ጡብ እቶ​ንም አሳ​ለ​ፋ​ቸው። በአ​ሞን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ። ዳዊ​ትም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።


በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡ​ብም፥ በእ​ር​ሻም ሥራ ሁሉ፥ በመ​ከ​ራም በሚ​ያ​ሠ​ሩ​አ​ቸው ሥራ ሁሉ፤ ሕይ​ወ​ታ​ቸ​ውን ያስ​መ​ር​ሩ​አ​ቸው ነበር።


የግ​ብ​ፅ​ንም ንጉሥ ፈር​ዖ​ንን፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም፥ መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ፥


እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪ​ያ​ዬን የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፤ ዙፋ​ኑ​ንም እኔ በሸ​ሸ​ግ​ኋ​ቸው በእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤ ጋሻ​ዎ​ቹ​ንም በእ​ነ​ርሱ ላይ ያነ​ሣል።


በጣ​ፍ​ና​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስን ጠላቱ ለሆ​ነው፥ ነፍ​ሱ​ንም ለፈ​ለ​ገው ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፌ እንደ ሰጠ​ሁት፥ እን​ዲሁ እነሆ የግ​ብ​ፅን ንጉሥ ፈር​ዖን ሖፍ​ራን ለጠ​ላ​ቶቹ፥ ነፍ​ሱ​ንም ለሚ​ፈ​ልጉ እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጡብን ወስ​ደህ በፊ​ትህ አኑ​ራት፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ከተማ ሥዕል ሣል​ባት፤


እኔም ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እንደ ዓመት በዓል ቀንም እንደ ገና በድ​ን​ኳን አስ​ቀ​ም​ጥ​ሃ​ለሁ።


ከብበው ያስጨንቁሻልና ውኃን ቅጂ፣ አምባሽን አጠንክሪ፣ ወደ ጭቃ ገብተሽ እርገጪ፣ የጡብን መሠሪያ ያዢ።


ወደ እኛም መጣና የጳ​ው​ሎ​ስን መታ​ጠ​ቂያ አን​ሥቶ እጁ​ንና እግ​ሩን በገዛ እጁ አስሮ እን​ዲህ አለ፥ “መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ይላል፤ የዚ​ህን መታ​ጠ​ቂያ ጌታ አይ​ሁድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲህ ያስ​ሩ​ታል፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል።”


አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች