Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 38:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አለ​ቆቹ ግን እኔ ከአ​ንተ ጋር እንደ ተነ​ጋ​ገ​ርሁ ቢሰሙ፥ ወደ አን​ተም መጥ​ተው፦ ለን​ጉሡ ያል​ኸ​ውን ንገ​ረን፤ አት​ሸ​ሽ​ገ​ንም፤ እኛም አን​ገ​ድ​ል​ህም፤ ደግሞ ንጉሡ ያለ​ህን ንገ​ረን ቢሉህ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 መኳንንቱ ከአንተ ጋራ እንደ ተነጋገርሁ ሰምተው ወደ አንተ ቢመጡና፣ ‘ንጉሡን ምን እንዳልኸው፣ ንጉሡም ምን እንዳለህ ንገረን፤ ሳትደብቅ ንገረን፤ አለዚያ እንገድልሃለን’ ቢሉህ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አለቆቹ ግን እኔ ከአንተ ጋር እንደተነጋገርሁ ቢሰሙ፥ ወደ አንተም መጥተው፦ ‘ለንጉሡ ያልኸው ምንድነው? ንገረን አትሸሽገንም፥ እኛም አንገድልህም፤ ንጉሡስ ለአንተ ምን አለህ?’ ንገረን ቢሉህ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ባለ ሥልጣኖቹ እኔ ከአንተ ጋር መነጋገሬን የሰሙ እንደ ሆነ መጥተው ምን እንደ ተባባልን ይጠይቁሃል፤ ሁሉን ነገር ባትነግራቸው እንገድልሃለን ብለው ያስፈራሩሃል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አለቆቹ ግን እኔ ከአንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ ቢሰሙ፥ ወደ አንተም መጥተው፦ ለንጉሡ ያልኸውን ንገረን አትሸሽገንም፥ እኛም አንገድልህም፥ ደግሞ ንጉሡ ያለህን ንገረን ቢሉህ፥ አንተ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 38:25
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም ለሴ​ቲቱ መልሶ፥ “የም​ጠ​ይ​ቅ​ሽን ነገር አት​ሰ​ው​ሪኝ” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ይና​ገር” አለች።


ሴዴ​ቅ​ያ​ስም ኤር​ም​ያ​ስን እን​ዲህ አለው፥ “ይህን ቃል ማንም አይ​ወቅ፥ አን​ተም አት​ሞ​ትም።


አለ​ቆ​ቹም ሁሉ ወደ ኤር​ም​ያስ መጥ​ተው ጠየ​ቁት፤ ንጉ​ሡም እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ደ​ዚህ ቃል ሁሉ ነገ​ራ​ቸው። ነገ​ሩም አል​ተ​ሰ​ማ​ምና ከእ​ርሱ ጋር መነ​ጋ​ገ​ርን ተዉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች