Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 38:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መዱ ጐተ​ቱት፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድም አወ​ጡት፤ ኤር​ም​ያ​ስም በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እነርሱም በገመዱ ጐትተው ከጕድጓዱ አወጡት። ኤርምያስም በዘበኞች አደባባይ ሰነበተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ኤርምያስንም በገመዱ ጐተቱት፤ ከጉድጓድም አወጡት፤ ኤርምያስም በእስር ቤት አደባባይ ተቀመጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እነርሱም ከዚያ ጒድጓድ ውስጥ በዚያው ገመድ ስበው አወጡኝና በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ዘጉብኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ኤርምያስንም በገመዱ ጐተቱት ከጕድጓድም አወጡት፥ ኤርምያስም በግዞት ቤት አደባባይ ተቀመጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 38:13
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ዴ​ዎ​ችም ሲያ​ልፉ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ ጐት​ተው አወ​ጡት፤ ለይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ዮሴ​ፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነ​ር​ሱም ዮሴ​ፍን ወደ ግብፅ ወሰ​ዱት።


ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ በደ​ኅና እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ይህን ሰው በግ​ዞት አኑ​ሩት፤ የመ​ከ​ራም እን​ጀራ መግ​ቡት፤ የመ​ከ​ራም ውኃ አጠ​ጡት በሉ​አ​ቸው” አለ።


የኡ​ዛይ ልጅ ፋልል በማ​ዕ​ዘኑ አን​ጻር ያለ​ው​ንና በዘ​በ​ኞች አደ​ባ​ባይ አጠ​ገብ ከላ​ይ​ኛው የን​ጉሡ ቤት ወጥቶ የቆ​መ​ውን ግንብ ሠራ። ከእ​ር​ሱም በኋላ የፋ​ሮስ ልጅ ፈዳያ ሠራ።


አለ​ቆ​ቹና ሕዝ​ቡም ሁሉ ለካ​ህ​ና​ትና ለነ​ቢ​ያተ ሐሰት፥ “ይህ ሰው በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተና​ግ​ሮ​ና​ልና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም” አሉ።


በዚያ ጊዜም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት በነ​በ​ረው በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ታስሮ ነበር።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ አዘዘ፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በግ​ዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖ​ሩት፤ እን​ጀ​ራም ሁሉ ከከ​ተማ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እን​ጀራ ከውጪ ጋጋ​ሪ​ዎች እያ​መጡ ይሰ​ጡት ነበር። እን​ዲ​ሁም ኤር​ም​ያስ በግ​ዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀ​ምጦ ነበር።


ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ውም አቤ​ሜ​ሌክ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “እነ​ዚ​ህን ጨር​ቆች በብ​ብ​ትህ ከገ​መዱ በታች አድ​ርግ” አለው፤ ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲሁ አደ​ረገ።


ኤር​ም​ያ​ስም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተያ​ዘ​ች​በት ቀን ድረስ በግ​ዞት ቤቱ አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጠ።


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ወሰ​ዱት፤ በግ​ዞት ቤትም አደ​ባ​ባይ ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መል​ክያ ጕድ​ጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መድ አወ​ረ​ዱት። በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም፤ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።


ሬስ። አቤቱ፥ የነ​ፍ​ሴን ፍርድ ፈረ​ድህ፤ ሕይ​ወ​ቴ​ንም ተቤ​ዥህ።


“እን​ኪ​ያስ ከሳ​ሾ​ችህ ሲመጡ እን​ሰ​ማ​ሃ​ለን” አለው፤ በሄ​ሮ​ድ​ስም ግቢ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቁት አዘዘ።


ሁለት ዓመ​ትም ካለፈ በኋላ፥ ፊል​ክስ ተሻ​ረና ጶር​ቅ​ዮስ ፊስ​ጦስ የሚ​ባል ሌላ ሀገረ ገዢ በእ​ርሱ ቦታ መጣ፤ ፊል​ክ​ስም በግ​ልጥ ለአ​ይ​ሁድ ሊያ​ዳላ ወደደ፤ ስለ​ዚ​ህም ጳው​ሎ​ስን እንደ ታሰረ ተወው።


ወደ ሮሜም በገ​ባን ጊዜ የመቶ አለ​ቃው እስ​ረ​ኞ​ችን ለሠ​ራ​ዊቱ አለቃ አስ​ረ​ከበ፤ ጳው​ሎስ ግን ከሚ​ጠ​ብ​ቀው አንድ ወታ​ደር ጋር ለብ​ቻው ይቀ​መጥ ዘንድ ፈቀ​ደ​ለት።


ጳው​ሎ​ስም በገ​ን​ዘቡ በተ​ከ​ራ​የው ቤት ሁለት ዓመት ተቀ​መጠ፤ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ሁሉ ይቀ​በል ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች