Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 29:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ኤር​ም​ያ​ስም የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ባቢ​ሎን በላ​ካ​ቸው በሳ​ፋን ልጅ በኤ​ል​ዓ​ሣና በኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ በገ​ማ​ርያ እጅ ደብ​ዳ​ቤ​ውን እን​ዲህ ሲል ላከው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ደብዳቤውንም ከይሁዳ ንጉሥ ከሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር በተላኩት መልእክተኞች በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ላከው፤ ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኤርምያስ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን ላከው፤ እንዲህም የሚል ነበር፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ደብዳቤውንም የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላካቸው በሻፋን ልጅ በኤልዓሳና በሕልቂያ ልጅ በገማርያ እጅ ላክሁት፤ የደብዳቤውም ፍሬ ነገር እንዲህ የሚል ነው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ኤርምያስ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን እንዲህ ሲል ላከው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 29:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም ጠሩ፤ የቤ​ቱም አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም ጸሓ​ፊ​ውም ሳም​ናስ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነ​ርሱ ወጡ።


ንጉ​ሡም ካህ​ኑን ኬል​ቅ​ያ​ስን፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ አኪ​ቃ​ምን፥ የሚ​ክ​ዩ​ንም ልጅ ዓክ​ቦ​ርን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳፋ​ንን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ብላ​ቴና ዓስ​ያን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦


ታላቁ ካህ​ንም ኬል​ቅ​ያስ ጸሓ​ፊ​ውን ሳፋ​ንን፥ “የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አግ​ኝ​ቻ​ለሁ” አለው፤ ኬል​ቅ​ያ​ስም መጽ​ሐ​ፉን ለሳ​ፋን ሰጠው፥ እር​ሱም አነ​በ​በው።


አዛ​ር​ያ​ስም ኬሌ​ስን ወለደ፤ ኬሌ​ስም ኤል​ዓ​ሳን ወለደ፤


ሳሎ​ምም ኬል​ቅ​ያ​ስን ወለደ፤ ኬል​ቅ​ያ​ስም ዓዛ​ር​ያ​ስን ወለደ፤


ንጉ​ሡም ኬል​ቅ​ያ​ስን፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ አኪ​ቃ​ምን፥ የሚ​ክ​ያ​ስ​ንም ልጅ አብ​ዶ​ንን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳፋ​ንን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ብላ​ቴና ዔሴ​ኢ​ያን፦


ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ቄም ሰዎ​ችን ወደ ግብፅ ላከ፤ የአ​ክ​ቦ​ርን ልጅ ኤል​ና​ታ​ንን፥ ሌሎ​ች​ንም ሰዎች ከርሱ ጋራ ወደ ግብፅ ላካ​ቸው።


ነገር ግን በሕ​ዝቡ እጅ እን​ዳ​ይ​ሰ​ጥና እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉት የሳ​ፋን ልጅ የአ​ኪ​ቃም እጅ ከኤ​ር​ም​ያስ ጋር ነበ​ረች።


ነገር ግን ኤል​ና​ታ​ንና ጎዶ​ልያ፥ ገማ​ር​ያም ክር​ታ​ሱን እን​ዳ​ያ​ቃ​ጥል ንጉ​ሡን ለመ​ኑት፤ እርሱ ግን አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ከግ​ዞት ቤቱ አደ​ባ​ባይ አወ​ጡት፤ ወደ ቤቱም ይወ​ስ​ደው ዘንድ ለሳ​ፋን ልጅ ለአ​ኪ​ቃም ልጅ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ሰጡት፤ እን​ዲ​ህም በሕ​ዝብ መካ​ከል ተቀ​መጠ።


በፊ​ታ​ቸ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰባ ሰዎ​ችና የሳ​ፋን ልጅ ያእ​ዛ​ንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በእጁ ጥና​ውን ይዞ ነበር፥ የዕ​ጣ​ኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች