Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 27:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስለ ቀሩት ዕቃ​ዎች የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በኢየሩሳሌምም ስለ ቀሩት ዕቃዎች፣ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በጌታ ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ስለ ቀሩት ዕቃዎች የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “በኢየሩሳሌም፥ በቤተ መቅደሱና በቤተ መንግሥቱ ስለ ቀሩት ዕቃዎች ሁሉ የእስራኤል አምላክ የሆንኩ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የምናገረውን ቃል ስሙ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም ስለ ቀረችው ዕቃ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 27:21
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ በቤ​ትህ ያለው ሁሉ፥ አባ​ቶ​ች​ህም እስከ ዛሬ ያከ​ማ​ቹት ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን የሚ​ፈ​ል​ስ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ምንም አይ​ቀ​ርም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላ​ቁ​ንና ታና​ሹን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የአ​ለ​ቆ​ቹ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ወሰደ።


የወ​ር​ቁና የብሩ ዕቃ​ዎች ሁሉ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሁሉ ሲሳ​ብ​ሳር ከባ​ቢ​ሎን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ከተ​መ​ለሱ ምር​ኮ​ኞች ጋር ወሰደ።


ንጉሡ ቂሮ​ስም ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወስዶ በአ​ም​ላኩ ቤት ያኖ​ራ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መቅ​ደስ ዕቃ​ዎች አወጣ።


እነሆ፥ በቤ​ትህ ያለው ሁሉ፥ አባ​ቶ​ች​ህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከ​ማ​ቹት ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን የሚ​ፈ​ል​ስ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ምንም አያ​ስ​ቀ​ሩ​ል​ህም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የዚ​ች​ንም ከተማ ኀይል ሁሉ፥ ጥሪ​ቷ​ንም ሁሉ፥ ክብ​ር​ዋ​ንም ሁሉ፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ነገ​ሥ​ታት መዝ​ገብ ሁሉ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ርሱ ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ይዘ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ያስ​ገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል።


“የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ ኢኮ​ን​ያ​ን​ንና የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አለ​ቆች ሁሉ ማርኮ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ባፈ​ለ​ሳ​ቸው ጊዜ፥


ወደ ባቢ​ሎን ይወ​ሰ​ዳሉ፤ እስ​ከ​ም​ጐ​በ​ኛ​ቸው ቀን ድረስ በዚያ ይኖ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በዚ​ያን ጊዜም ትወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ።”


ዮድ። አስ​ጨ​ና​ቂው በም​ኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባ​ኤህ እን​ዳ​ይ​ገቡ ያዘ​ዝ​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ወደ መቅ​ደ​ስዋ ሲገቡ አይ​ታ​ለ​ችና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች