Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 27:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሐሰ​ተ​ኛን ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አት​ገ​ዙም የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል አት​ስሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሐሰተኛ ትንቢት ስለሚነግሯችሁ፣ ‘የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም’ የሚሏችሁን ነቢያት አትስሙ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሐሰተኛን ትንቢት ለእናንተ በመናገር፦ ‘ለባቢሎን ንጉሥ አታገለግሉም’ የሚሉአችሁን የነቢያትን ቃላት አትስሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ለባቢሎን ንጉሥ አትገዙም፥ ብለው የሚነግሩአችሁን የነቢያት ቃል አትስሙ፤ እነርሱ የሚናገሩት የሐሰት ትንቢት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሐሰተኛን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ አትገዙም የሚሉአችሁን የነቢያትን ቃል አትስሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 27:14
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ነቢ​ያቱ በስሜ የሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፤ አላ​ክ​ኋ​ቸ​ውም፤ አላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውም፤ አል​ተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውም፤ የሐ​ሰ​ቱን ራእይ፥ ምዋ​ር​ት​ንም፥ ከን​ቱ​ንም ነገር፥ በል​ባ​ቸ​ውም የፈ​ጠ​ሩ​ትን ይተ​ነ​ብ​ዩ​ላ​ች​ኋል።”


“እኔ ሳል​ል​ካ​ቸው እነ​ዚህ ነቢ​ያት ሮጡ፤ እኔም ሳል​ነ​ግ​ራ​ቸው ትን​ቢ​ትን ተና​ገሩ።


ሕል​ምን አለ​ምን እያሉ በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን የነ​ቢ​ያ​ትን ነገር ሰም​ቻ​ለሁ።


ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ሐና​ን​ያን፥ “ሐና​ንያ ሆይ ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ላ​ከ​ህም፤ ነገር ግን ይህ ሕዝብ በሐ​ሰት እን​ዲ​ታ​መን አድ​ር​ገ​ሃል።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በእ​ና​ን​ተና በዚ​ህች ሀገር አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም ብለው ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ የነ​በሩ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችሁ ወዴት አሉ?


እነሆ በይ​ሁዳ ቤት የቀ​ሩ​ትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ያወ​ጣሉ፤ እነ​ዚ​ያም ሴቶች፦ ባለ​ሟ​ሎ​ችህ አታ​ል​ለ​ው​ሃል፤ አሸ​ን​ፈ​ው​ህ​ማል፤ እግ​ሮ​ችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ከገቡ እነ​ርሱ ከአ​ንተ ወደ ኋላ ተመ​ል​ሰ​ዋል ይላሉ።


ኖን። ነቢ​ያ​ትሽ ከን​ቱና ዕብ​ደ​ትን አይ​ተ​ው​ል​ሻል፤ ምር​ኮ​ሽን ይመ​ልሱ ዘንድ በደ​ል​ሽን አል​ገ​ለ​ጡም፤ ከን​ቱና የማ​ይ​ረባ ነገ​ር​ንም አይ​ተ​ው​ል​ሻል።


ነፋስንም ተከትሎ፦ ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል።


ተራፊም ከንቱነትን ተናግረዋልና፥ ምዋርተኞችም ውሸትን አይተዋልና፣ ሕልምንም የሚያዩ በሐሰት ተናግረዋል፥ በከንቱም ያጽናናሉ፣ እረኛም የላቸውምና እንደ በጎች ተቅበዝብዘዋል ተጨንቀውማል።


“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።


ከው​ሾች ተጠ​በቁ፤ ከክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችም ተጠ​በቁ፤ ሥጋ​ቸ​ውን ብቻ በመ​ቍ​ረጥ ተገ​ዝ​ረ​ናል ከሚ​ሉም ተጠ​በቁ።


ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች