Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 27:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከም​ድ​ራ​ችሁ እን​ዲ​ያ​ር​ቁ​አ​ችሁ፥ እኔም እን​ዳ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ፥ እና​ን​ተም እን​ድ​ት​ጠፉ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከምድራችሁ እንድትፈናቀሉ፣ እኔም እንዳሳድዳችሁና እንዳጠፋችሁ የሐሰት ትንቢት ይነግሯችኋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከምድራቸሁ እንድትርቁ፥ እኔም እንዳሳድዳችሁ እናንተም እንድትጠፉ ሐሰተኛ ትንቢትን ይነግሩአችኋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነርሱ ለእናንተ የሚናገሩት ትንቢት የሐሰት ትንቢት ነው፤ ከትውልድ አገራችሁ ወደ ሩቅ አገር ትወሰዳላችሁ፤ እኔም ስለማሳድዳችሁ ትጠፋላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከምድራቸሁ እንዲያርቁአችሁ፥ እኔም እንዳሳድዳችሁ እናንተም እንድትጠፉ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 27:10
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ከመ​ተ​ተኛ ጋር አንድ አት​ሁኑ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ነቢ​ያቱ በስሜ የሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፤ አላ​ክ​ኋ​ቸ​ውም፤ አላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውም፤ አል​ተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውም፤ የሐ​ሰ​ቱን ራእይ፥ ምዋ​ር​ት​ንም፥ ከን​ቱ​ንም ነገር፥ በል​ባ​ቸ​ውም የፈ​ጠ​ሩ​ትን ይተ​ነ​ብ​ዩ​ላ​ች​ኋል።”


ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል አት​ስሙ፤ ከን​ቱ​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ሳይ​ሆን ከገዛ ልባ​ቸው የወ​ጣ​ውን ራእይ ይና​ገ​ራሉ።


ሕል​ምን አለ​ምን እያሉ በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን የነ​ቢ​ያ​ትን ነገር ሰም​ቻ​ለሁ።


ሐሰ​ተ​ኛን ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አት​ገ​ዙም የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል አት​ስሙ።


እኔ አል​ላ​ክ​ኋ​ቸ​ው​ምና፤ ነገር ግን እኔ እን​ዳ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ፥ እና​ን​ተና ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ ነቢ​ያ​ትም እን​ድ​ት​ጠፉ በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


ለካ​ህ​ና​ትም ለዚ​ህም ሕዝብ እን​ዲህ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃ በቅ​ርብ ጊዜ ከባ​ቢ​ሎን ይመ​ለ​ሳል የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ቃል አት​ስሙ።


ሐና​ን​ያም በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ግ​ዲህ በሁ​ለት ዓመት ውስጥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ የና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን ቀን​በር ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ አን​ገት እሰ​ብ​ራ​ለሁ” አለ። ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም መን​ገ​ዱን ሄደ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስ​ወ​ግ​ድ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፅን ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና በዚህ ዓመት ትሞ​ታ​ለህ” አለው።


ከፊቴ አስ​ወ​ግ​ዳት ዘንድ ይህች ከተማ ከሠ​ሩ​አት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በቁ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ ውስጥ ናትና፤


እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን የለ​ምን? ወይስ ንጉ​ሥዋ በእ​ር​ስዋ ዘንድ የለ​ምን? የሚል የወ​ገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ሀገር ተሰማ። በተ​ቀ​ረፁ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውና በባ​ዕድ ከን​ቱ​ነ​ትስ ያስ​ቈ​ጡኝ ስለ ምን​ድን ነው?


ኖን። ነቢ​ያ​ትሽ ከን​ቱና ዕብ​ደ​ትን አይ​ተ​ው​ል​ሻል፤ ምር​ኮ​ሽን ይመ​ልሱ ዘንድ በደ​ል​ሽን አል​ገ​ለ​ጡም፤ ከን​ቱና የማ​ይ​ረባ ነገ​ር​ንም አይ​ተ​ው​ል​ሻል።


ተራፊም ከንቱነትን ተናግረዋልና፥ ምዋርተኞችም ውሸትን አይተዋልና፣ ሕልምንም የሚያዩ በሐሰት ተናግረዋል፥ በከንቱም ያጽናናሉ፣ እረኛም የላቸውምና እንደ በጎች ተቅበዝብዘዋል ተጨንቀውማል።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእ​ሳት የሚ​ሠዋ፥ ምዋ​ር​ተ​ኛም፥ ሞራ ገላ​ጭም፥ አስ​ማ​ተ​ኛም፥ መተ​ተ​ኛም፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች