Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 22:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዘ​መኑ አይ​ከ​ና​ወ​ን​ምና፥ ከዘ​ሩም በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ አይ​ነ​ሣ​ምና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ለይ​ሁዳ ገዢ አይ​ሾ​ም​ምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠ​ሪው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣ አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤ በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣ መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 “ይህ ሰው ልጆቹን ሁሉ አጥቶ ኑሮው የማይሳካለት እንዲሆን ተፈርዶበታል፤ የዳዊትን ዙፋን ለመውረስ በይሁዳ የሚነግሡ ዘሮች አይተርፉለትም ብለሽ መዝግቢ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወን በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ እንግዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 22:30
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሕ​ዝቡ መካ​ከል የሚ​ራ​ራ​ለት የለም፤ ቤቱ ከሰ​ማይ በታች አይ​ቀ​ር​ለ​ትም።


እረ​ኞች አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ት​ምና፤ ስለ​ዚ​ህም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ውን አላ​ወ​ቁም፤ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተበ​ት​ነ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስ​ፋ​ሽን አስ​ቈ​ር​ጦ​ሻ​ልና፥ በእ​ር​ሱም አይ​ከ​ና​ወ​ን​ል​ሽ​ምና እጅ​ሽን በራ​ስሽ ላይ አድ​ር​ገሽ ከዚያ ደግሞ ትወ​ጫ​ለሽ።


በዳ​ዊት ዙፋን የም​ት​ቀ​መጥ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ! አን​ተና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በእ​ነ​ዚ​ህም በሮች የሚ​ገባ ሕዝ​ብህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሔ​ል​ማ​ዊ​ውን ሸማ​ያ​ንና ዘሩን እቀ​ጣ​ለሁ፤ እኔም ለሕ​ዝቤ የማ​ደ​ር​ገ​ውን መል​ካ​ሙን ነገር የሚ​ያይ ሰው በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አይ​ኖ​ር​ላ​ቸ​ውም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፃን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።”


ስለ​ዚ​ህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​አ​ቄም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዳ​ዊት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጥ ልጅ አይ​ኖ​ር​ለ​ትም፥ ሬሳ​ውም በቀን ለት​ኩ​ሳት፥ በሌ​ሊ​ትም ለው​ርጭ ይጣ​ላል።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስን ልጆች በፊቱ ገደ​ላ​ቸው፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች ሁሉ ደግሞ በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች