Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 22:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 አን​ተ​ንም፥ የወ​ለ​ደ​ች​ህን እና​ት​ህ​ንም ወዳ​ል​ተ​ወ​ለ​ዳ​ች​ሁ​ባት ወደ ሌላ ሀገር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 አንተንና የወለደችህን እናትህን ወዳልተወለዳችሁበት ወደ ሌላ አገር ወርውሬ እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 አንተንም የወለደችህንም እናትህን ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ አገር እጥላችኋለሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 አንተንም፥ የወለደችህ እናትህንም እንድትሰደዱ አደርጋለሁ፤ ማንኛችሁም ወዳልተወለዳችሁበት አገር ሄዳችሁ ሁላችሁም እዚያ ትሞታላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 አንተንም የወለደችህንም እናትህን ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ አገር እጥላችኋለሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 22:26
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮአ​ኪ​ን​ንም ወደ ባቢ​ሎን አፈ​ለሰ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም እናት፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሚስ​ቶች፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ቹ​ንም፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ታላ​ላ​ቆች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ማረከ።


ዮአ​ኪ​ንም በነ​ገሠ ጊዜ ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ወር ነገሠ፤ እና​ቱም ኒስታ ትባል ነበር፤ እር​ስ​ዋም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰው የኤ​ል​ና​ታን ልጅ ነበ​ረች።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የይ​ሁዳ ንጉሥ ዮአ​ኪን በተ​ማ​ረከ በሠ​ላሳ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ዮር​ማ​ሮ​ዴቅ በነ​ገሠ በአ​ን​ደ​ኛው ዓመት የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ዮአ​ኪ​ንን ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ከወ​ህኒ ቤትም አወ​ጣው፤


በወ​ህ​ኒም ውስጥ ለብ​ሶት የነ​በ​ረ​ውን ልብስ ለወ​ጠ​ለት፤ ዮአ​ኪ​ንም በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ በፊቱ ሁል​ጊዜ እን​ጀራ ይበላ ነበር።


ቀለ​ቡ​ንም ሁል​ጊዜ ከን​ጉሡ ቤት ይቀ​በል ነበር፤ በሕ​ይ​ወ​ቱም ዘመን ሁሉ የዘ​ወ​ትር ቀለ​ቡን ዕለት ዕለት ይሰ​ጡት ነበር።


እነሆ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ይል ወር​ውሮ ይጥ​ል​ሃል፤ ያጠ​ፋ​ሃ​ልም፤ ልብ​ስ​ህ​ንና የክ​ብር አክ​ሊ​ል​ህ​ንም ይገ​ፍ​ሃል፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ በም​ድ​ሪቱ የሚ​ኖ​ሩ​ትን በመ​ከራ አሰ​ና​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ሽም እን​ዲ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ለነ​ገ​ሥ​ታ​ቱና ለመ​ኳ​ን​ንቱ፦ የክ​ብ​ራ​ችሁ አክ​ሊል ከራ​ሳ​ችሁ ወር​ዶ​አ​ልና ራሳ​ች​ሁን አዋ​ር​ዳ​ችሁ ተቀ​መጡ በላ​ቸው።


ስለ​ዚህ ከዚች ምድር እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ አላ​ወ​ቃ​ች​ኋት ምድር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ምሕ​ረ​ትን ለማ​ያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ ሌሎች አማ​ል​ክት ቀንና ሌሊት ታገ​ለ​ግ​ላ​ላ​ችሁ።”


ነፍ​ሳ​ች​ሁም ወደ​ም​ት​መ​ኛት ወደ​ዚ​ያች ምድር አት​መ​ለ​ሱም።


ወደ ባቢ​ሎ​ንም የሄ​ዱ​ትን የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ ኢኮ​ን​ያ​ን​ንና የይ​ሁ​ዳን ምርኮ ሁሉ ወደ​ዚች ስፍራ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ቀን​በር እሰ​ብ​ራ​ለ​ሁና።”


ይህም የሆ​ነው ንጉሡ ኢኮ​ን​ያ​ንና እቴ​ጌ​ዪቱ፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ቹም፥ የይ​ሁ​ዳና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አለ​ቆች ነጻ​ዎ​ችና እሥ​ረ​ኞች፥ ብል​ሃ​ተ​ኞ​ችና ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ችም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከወጡ በኋላ ነው።


በዚያ ለመ​ቀ​መጥ በል​ባ​ቸው ተስፋ ወደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለሱ ዘንድ በግ​ብፅ ለመ​ኖር ከመጡ ከይ​ሁዳ ቅሬታ ወገን የሚ​ያ​መ​ል​ጥና የሚ​ቀር፥ ወደ​ዚ​ያም የሚ​መ​ለስ አይ​ኖ​ርም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጥም በቀር ማንም አይ​መ​ለ​ስም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች