Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 18:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ያደ​ረ​ገ​ች​ውን በጣም የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን ነገር የሚ​ሰ​ሙት እን​ዳለ አሕ​ዛ​ብን ጠይቁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስኪ አሕዛብን፣ ‘እንዲህ ዐይነት ነገር በመካከላችሁ ተሰምቶ ያውቃል?’ ብላችሁ ጠይቁ። ድንግሊቱ እስራኤል፣ እጅግ ክፉ ነገር አድርጋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ በአሕዛብ መካከል፦ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? ብላችሁ ጠይቁ። የእስራኤል ድንግል በጣም የሚያስደነግጠውን ነገር አድርጋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን የመሰለ ነገር በሕዝቦች መካከል ተሰምቶ እንደ ሆነ ጠይቁ፤ የተለዩ የእስራኤል ሕዝብ በጣም አጸያፊ የሆነ ነገር አድርገዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአሕዛብ መካከል፦ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? ብላችሁ ጠይቁ። የእስራኤል ድንግል በጣም የሚያስደነግጠውን ነገር አድርጋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 18:13
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቤቱ አዛዥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ የሠ​ራ​ዊቱ ጸሓፊ ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጡ፤ የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ቃል ነገ​ሩት።


ከቶ እን​ዲህ ያለ ነገ​ርን ማን ሰም​ቶ​አል? እን​ዲ​ህስ ያለ ነገ​ርን ማን አይ​ቶ​አል? በውኑ ሀገር በአ​ንድ ቀን ታም​ጣ​ለ​ችን? ወይስ በአ​ንድ ጊዜ ሕዝብ ይወ​ለ​ዳ​ልን? ጽዮን እን​ዳ​ማ​ጠች ወዲ​ያው ልጆ​ች​ዋን ወል​ዳ​ለ​ችና።


“እን​ደ​ዚ​ህም ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የወ​ገኔ ልጅ ድን​ግ​ሊቱ በታ​ላቅ ስብ​ራ​ትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ ሌሊ​ትና ቀን ሳያ​ቋ​ርጡ እን​ባን ያፍ​ስሱ።


ምንጭ ከዓ​ለት ይጠ​ፋ​ልን? በረ​ዶስ ከሊ​ባ​ኖስ ይጠ​ፋ​ልን? ወራጅ ውኃስ በኀ​ይ​ለኛ ነፋስ ይመ​ለ​ሳ​ልን?


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ነቢ​ያት ላይ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ዝ​ራሉ፤ በሐ​ሰ​ትም ይሄ​ዳሉ፤ ማንም ከክ​ፋቱ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን እጅ ያበ​ረ​ታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እንደ ገሞራ ሆኑ​ብኝ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ሆይ እንደ ገና እሠ​ራ​ሻ​ለሁ፤ አን​ቺም ትሠ​ሪ​ያ​ለሽ፤ እንደ ገናም ከበ​ሮ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ከዘ​ፋ​ኞች ጋር ትወ​ጫ​ለሽ።


የም​ት​ሰ​ቀ​ጥ​ጥና የም​ታ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ነገር በም​ድር ላይ ሆና​ለች፤


ሳም​ኬት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀያ​ላ​ኖ​ችን ሁሉ ከመ​ካ​ከሌ አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው፤ ምር​ጦ​ችን ያደ​ቅቅ ዘንድ ጊዜን ጠራ​ብኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ግ​ሊ​ቱን የይ​ሁ​ዳን ልጅ በመ​ጭ​መ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ጨ​መቅ ወይን ረገ​ጣት። ስለ​ዚ​ህም አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።


በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት የሚ​ያ​ሰ​ፈ​ራን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ በዚያ የኤ​ፍ​ሬ​ም​ንም ዝሙት አየሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ረክ​ሶ​አል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ና​ንተ ላይ ለሙሾ የማ​ነ​ሣ​ውን ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ወደ​ቀች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ነ​ሣም፤ በም​ድ​ርዋ ላይ ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ትም የለም።


በእ​ና​ንተ ላይ ዝሙት ይሰ​ማል፤ እን​ደ​ዚህ ያለው ዝሙ​ትም አረ​ማ​ው​ያን እንኳ የማ​ያ​ደ​ር​ጉት ነው፤ ያባ​ቱን ሚስት ያገባ አለና።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ፈር​ተው፥ “አማ​ል​ክት ወደ እነ​ርሱ ወደ ሰፈር መጥ​ተ​ዋል” አሉ። ደግ​ሞም እን​ዲህ አሉ፥ “ወዮ​ልን! አቤቱ፥ ዛሬ አድ​ነን፤ ከዚህ አስ​ቀ​ድሞ እን​ዲህ ያለ ነገር አል​ሆ​ነ​ምና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች