Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በፊቴ ክፉን ነገር ቢያ​ደ​ርጉ ቃሌ​ንም ባይ​ሰሙ፥ እኔ አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ስለ ተና​ገ​ር​ሁት መል​ካም ነገር እጸ​ጸ​ታ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በፊቴ ክፉ ነገር ቢያደርግና ባይታዘዘኝ፣ አደርግለታለሁ ብዬ ያሰብሁትን መልካም ነገር አስቀርበታለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በፊቴ ክፉን ነገር ቢያደርግ ድምፄንም ባይሰማ፥ እኔ ላደርግለት ስለ ተናገርሁት መልካም ነገር እጸጸታለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ያ ሕዝብ ለእኔ የማይታዘዝና ክፋትንም የሚያደርግ ሆኖ ከተገኘ ላደርግለት ያቀድኩትን መልካም ነገር አላደርግለትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በፊቴ ክፉን ነገር ቢያደርግ ቃሌንም ባይሰማ፥ እኔ አደርግለት ዘንድ ስለ ተናገርሁት መልካም ነገር እጸጸታለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 18:10
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በል​ቅሶ የሚ​ዘሩ በደ​ስታ ይሰ​በ​ስ​ባሉ።


ጻድቁ ግን ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ቢሠራ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ገው ርኵ​ሰት ሁሉ ቢያ​ደ​ርግ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልን? የሠ​ራው ጽድቅ ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም፤ በአ​ደ​ረ​ገው ዐመ​ፅና በሠ​ራት ኀጢ​አት በዚ​ያች ይሞ​ታል።


አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የሕ​ዝ​ብ​ህን ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ በበ​ደ​ለ​በት ቀን የጻ​ድቅ ጽድቁ አያ​ድ​ነ​ውም፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛም ከኀ​ጢ​አቱ በተ​መ​ለ​ሰ​በት ቀን በኀ​ጢ​አቱ አይ​ሰ​ና​ከ​ልም፤ ጻድ​ቁም ኀጢ​አት በሠ​ራ​በት ቀን በጽ​ድቁ በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም።


ጻድቅ ከጽ​ድቁ ተመ​ልሶ ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ ይሞ​ት​በ​ታል።


ከወ​ሩም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን እን​ዲሁ አድ​ርግ፤ ይኸ​ውም ስለ ሳተ​ውና ስለ በደ​ለው ሁሉ ነው። እን​ዲሁ ስለ ቤቱ አስ​ተ​ስ​ርዩ።


እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፥ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።


በግ​ብፅ ምድ​ርና በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴ​ንና ክብ​ሬን ያዩ እነ​ዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥


በእ​ው​ነት ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር አያ​ዩም፤ ከእኔ ጋር በዚህ ላሉ መል​ካ​ም​ንና ክፉን ለይ​ተው ለማ​ያ​ውቁ ልጆ​ቻ​ቸው፥ የሚ​ያ​ው​ቀው ለሌለ ለታ​ናሹ ሁሉ ያችን ሀገር እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለጥ​ፋት ያነ​ሳ​ሱኝ ሁሉ አያ​ዩ​አ​ትም።


ምድ​ሪ​ቱን እንደ ሰለ​ሉ​ባ​ቸው እንደ እነ​ዚያ አርባ ቀኖች ቍጥር ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ አር​ባው ቀን አርባ ዓመት፥ አንዱ ቀንም አንድ ዓመት ይሁ​ን​ባ​ችሁ፤ እን​ግ​ዲህ የቍ​ጣ​ዬን መቅ​ሠ​ፍት ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “በድ​ለ​ኻል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ህን ትእ​ዛ​ዙን አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና፤ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ት​ህን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጽ​ን​ቶ​ልህ ነበር።


“ሳኦል እኔን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሶ​አ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም አል​ፈ​ጸ​መ​ምና ስላ​ነ​ገ​ሥ​ሁት ተጸ​ጸ​ትሁ።” ሳሙ​ኤ​ልም አዘነ። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


ሳሙ​ኤ​ልም እስከ ሞተ​በት ቀን ድረስ ሳኦ​ልን ለማ​የት ዳግ​መኛ አል​ሄ​ደም፤ ሳሙ​ኤ​ልም ለሳ​ኦል አለ​ቀሰ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሳኦ​ልን ስላ​ነ​ገሠ ተጸ​ጸተ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ው​ነት ቤትህ፥ የአ​ባ​ት​ህም ቤት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊቴ እን​ዲ​ኖር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያከ​በ​ሩ​ኝን አከ​ብ​ራ​ለ​ሁና፥ የና​ቁ​ኝም ይና​ቃ​ሉና ይህ አይ​ሆ​ን​ል​ኝም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች