Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ለዚ​ህም ሕዝብ የተ​መ​ሸገ የናስ ቅጥር አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ይዋ​ጉ​ሃል፤ እኔ ግን ለማ​ዳን ከአ​ንተ ጋር ነኝና አያ​ሸ​ን​ፉ​ህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ለዚህ ሕዝብ የናስ ቅጥር፣ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ልታደግህና፣ ላድንህም፣ እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና፤ ቢዋጉህም እንኳ፣ ሊያሸንፉህ አይችሉም፤” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ይዋጉሃል እኔ ግን ላድንህና ልታደግህ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም፥ ይላል ጌታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እነርሱን መቋቋም እንድትችል እንደ ነሐስ ግንብ አበረታሃለሁ፤ አንተን ለማዳንና ለመታደግ ከአንተ ጋር ስለ ሆንኩ አደጋ ቢጥሉብህም እንኳ አያሸንፉህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፥ ይዋጉሃል እኔ ግን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 15:20
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማ​ስ​ተ​ዋል ዘምሩ፤


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ጌታ ራሱ ምል​ክት ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እነሆ፥ ድን​ግል ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች፤ ስሙ​ንም አማ​ኑ​ኤል ብላ ትጠ​ራ​ዋ​ለች።


እኔ አድ​ንህ ዘንድ ከአ​ንተ ጋራ ነኝና ከፊ​ታ​ቸው የተ​ነሣ አት​ፍራ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እናቴ ሆይ! ለም​ድር ሁሉ የክ​ር​ክ​ርና የጥል ሰው የሆ​ን​ሁ​ትን እኔን ወል​ደ​ሽ​ኛ​ልና ወዮ​ልኝ! ለማ​ንም አል​ጠ​ቀ​ም​ሁም፤ ማንም እኔን አል​ጠ​ቀ​መ​ኝም፤ ከሚ​ረ​ግ​ሙ​ኝም የተ​ነሣ ኀይሌ አለቀ።


አቤቱ! አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ አስ​በኝ፤ ጐብ​ኘ​ኝም፤ ከሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝም አድ​ነኝ እንጂ፥ አት​ታ​ገ​ሣ​ቸው፤ ስለ አንተ እንደ ሰደ​ቡኝ አስብ።


ኤር​ም​ያ​ስም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተያ​ዘ​ች​በት ቀን ድረስ በግ​ዞት ቤቱ አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጠ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንን ስለ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል አዘ​ዘው፦


ከም​ት​ፈ​ሩት ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት አት​ፍሩ፤ አድ​ና​ችሁ ዘንድ፥ ከእ​ጁም አስ​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ እኔ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍሩ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በተ​ፈ​ታኝ ሕዝቤ መካ​ከል ፈታኝ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በፈ​ተ​ንሁ ጊዜ ታው​ቀ​ኛ​ለህ።


እነሆ ፊት​ህን በፊ​ታ​ቸው አጸ​ና​ሁት፤ ኀይ​ል​ህ​ንም ከኀ​ይ​ላ​ቸው ይልቅ አጸ​ና​ለሁ።


ሁል​ጊዜ ከዓ​ለት ይልቅ ትጸ​ና​ለህ፤ አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ፤ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።”


ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች