Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የሚ​ያ​ሳ​ዝ​ኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበ​ረ​ታሉ? ቍስ​ሌስ ስለ ምን የማ​ይ​ፈ​ወስ ሆነ? ስለ ምንስ አል​ሽ​ርም አለ? እንደ ሐሰ​ተኛ ምንጭ፥ እን​ዳ​ል​ታ​መ​ነች ውኃም ሆነ​ብኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሕመሜ ለምን ጸናብኝ? ቍስሌስ ለምን በረታብኝ? ለምንስ የማይፈወስ ሆነ? እንደሚያታልል ወንዝ፣ እንደሚያሳስት ምንጭ ትሆንብኛለህን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ለምን ሕመሜ የማያቋርጥ ሆነ? ቁስሌስ የማይፈወስ ለምን ሆነ? ለምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆንብኛለህን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሕመሜ የማይድነው፥ ቊስሌስ የማይጠገነውና የማይፈወሰው ለምንድን ነው? በበጋ ወራት እንደሚደርቅ ጅረት ተስፋ ታስቈርጠኛለህን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆነኛለህን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 15:18
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባሕር ይጐ​ድ​ላል፤ ወን​ዙም ይነ​ጥ​ፋል፤ ይደ​ር​ቅ​ማል።


ፍር​ዴን ሐሰ​ተኛ አደ​ረ​ገ​ብኝ፤ በደ​ልም ሳይ​ኖ​ር​ብኝ በግ​ፍዕ መከ​ራን እቀ​በ​ላ​ለሁ።


ነፍ​ሴም እጅግ ታወ​ከች፤ አን​ተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?


በውኑ ይሁ​ዳን ፈጽ​መህ ጥለ​ኸ​ዋ​ልን? ነፍ​ስ​ህስ ጽዮ​ንን ጠል​ታ​ታ​ለ​ችን? ስለ ምን መታ​ኸን? ፈው​ስስ ስለ ምን የለ​ንም? ስለ ምን ተስፋ አደ​ረ​ግን? ነገር ግን መል​ካም ነገር አል​ተ​ገ​ኘም፤ የፈ​ው​ስን ጊዜ ተስፋ አደ​ረ​ግን፤ ነገር ግን ድን​ጋጤ ሆነ።


ታላ​ላ​ቆ​ች​ዋም ብላ​ቴ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ውኃ ሰደዱ፤ ወደ ጕድ​ጓድ መጡ፤ ውኃም አላ​ገ​ኙም፤ ዕቃ​ቸ​ው​ንም ባዶ​ውን መለሱ፤ ዐፈ​ሩም፤ ተዋ​ረ​ዱም፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ተከ​ና​ነቡ።


ድካ​ም​ንና ጣርን አይ ዘንድ፥ ዘመ​ኔም በእ​ፍ​ረት ታልቅ ዘንድ ስለ ምን ከማ​ኅ​ፀን ወጣሁ?


አቤቱ! አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ እኔም ተታ​ለ​ልሁ፤ ከእ​ኔም በረ​ታህ አሸ​ነ​ፍ​ህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳ​ቂያ ሆኛ​ለሁ፤ ሁሉም ያፌ​ዙ​ብ​ኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስብ​ራ​ትህ የማ​ይ​ፈ​ወስ፥ ቍስ​ል​ህም ክፉ ነው።


ቍስ​ልህ የማ​ይ​ፈ​ወስ ሆኖ​አ​ልና ስለ ስብ​ራ​ትህ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ? በደ​ልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ት​ህም ስለ በዛ፥ ይህን አድ​ር​ጌ​ብ​ሃ​ለሁ።


ስለዚህ ትሎት ለሞሬሼትጌት ትሰጪአለሽ፥ የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት አታላይ ይሆናሉ።


ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች