ኤርምያስ 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እናንተንም ታቃጥላችኋለችና በማታውቀው ሀገር ለጠላቶችህ አስገዛሃለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ቍጣዬ በላያችሁ፣ የሚነድድ እሳት ትጭራለችና፣ በማታውቀው አገር፣ ለጠላቶችህ ባሪያ አደርግሃለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የምታቃጥላችሁ እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለችና ከጠላቶችህ ጋር ወደማታውቀው ምድር አሻግርሃለሁስ።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ቊጣዬ ሊጠፋ እንደማይችል እሳት ነው። ስለዚህ በባዕድ ሀገር የጠላቶቻችሁ ባሪያዎች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የምታቃጥላችሁ እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና ከጠላቶችህ ጋር ወደማታውቀው ምድር አሳልፍሃለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |