Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 13:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እን​ዲሁ የይ​ሁ​ዳን ትዕ​ቢት፥ ታላ​ቁ​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ትዕ​ቢት አበ​ላ​ሻ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የይሁዳን ትዕቢትና የኢየሩሳሌምን እብሪት እንደዚሁ አጠፋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “ጌታ እንዲህ ይላል፦ እንዲሁ የይሁዳን ትዕቢት ታላቁንም የኢየሩሳሌምን ትዕቢት አጠፋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “የይሁዳን ኲራትና የኢየሩሳሌምን ታላቅ ትዕቢት የማስወግደው በዚህ ዐይነት ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንዲሁ የይሁዳን ትዕቢት ታላቁንም የኢየሩሳሌምን ትዕቢት አበላሻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 13:9
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ።


የሞ​ዓ​ብን ትዕ​ቢ​ትና እጅግ መኵ​ራ​ቱን ሰም​ተ​ናል፤ ትዕ​ቢ​ቱ​ንም አስ​ወ​ገ​ድሁ፤ ጥን​ቈ​ላህ እን​ዲህ አይ​ደ​ለ​ምና፥ እን​ዲ​ህም አይ​ደ​ለም፤


የክ​ቡ​ራ​ንን ትዕ​ቢት ይሽር ዘንድ፥ የም​ድ​ር​ንም ክቡ​ራን ሁሉ ያዋ​ርድ ዘንድ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስ​ኖ​ታል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፤


ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ፈጽሞ ምድረ በዳ ይሆኑ ዘንድ፥ ለር​ግ​ማ​ንም አደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች፥ ነገ​ሥ​ታ​ቷ​ንም፥ አለ​ቆ​ች​ዋ​ንም አጠ​ጣ​ኋ​ቸው።


የሞ​አ​ብን ስድብ፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንም ብዙ ውር​ደ​ቱን፥ ልቡ​ና​ው​ንም ያስ​ታ​በ​የ​በ​ትን ትዕ​ቢ​ቱን ሰም​ተ​ናል።


ኰር​ተው ነበር፤ በፊ​ቴም ርኵስ ነገር አደ​ረጉ፤ ስለ​ዚህ እንደ አየሁ አስ​ወ​ገ​ድ​ኋ​ቸው።


እኅ​ትሽ ሰዶ​ምም በት​ዕ​ቢ​ትሽ ቀን በአ​ፍሽ አል​ተ​ወ​ሳ​ችም።


የት​ዕ​ቢ​ታ​ች​ሁን ስድብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሰማ​ያ​ች​ሁ​ንም እንደ ብረት፥ ምድ​ራ​ች​ሁ​ንም እንደ ናስ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ዘራፊዎች ዘርፈዋቸዋልና፥ የወይናቸውንም አረግ አጥፍተዋልና እግዚአብሔር የያዕቆብን ክብር እንደ እስራኤል ክብር ይመልሳል።


በዚያን ጊዜ እየታበዩ የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ርድ ይከ​ብ​ራ​ልና።”


ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል፤” ይላል።


እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች