Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 11:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በመ​ዓት እጐ​በ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ቸው በሰ​ይፍ ይሞ​ታሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በራብ ይሞ​ታሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ እኔ እቀጣቸዋለሁ፤ ጕልማሶቻቸው በሰይፍ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እቀጣቸዋለሁ፤ ጉልማሶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “እኔ ራሴ እቀጣቸዋለሁ፤ ጐልማሶቻቸው በሰይፍ ያልቃሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ጎበዛዝቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 11:22
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚ​ህም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ንጉሥ አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ እር​ሱም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን በቤተ መቅ​ደሱ ውስጥ በሰ​ይፍ ገደ​ላ​ቸው፤ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም አል​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ደና​ግ​ሉ​ንም አል​ማ​ረም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው።


ስለ​ዚህ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለራብ ስጥ፤ ለሰ​ይ​ፍም እጅ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ላድ መካ​ንና መበ​ለ​ቶች ይሁኑ፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ውም በሞት ይጥፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በጦ​ር​ነት ጊዜ በሰ​ይፍ ይመቱ።


እንደ ሥራ​ች​ሁም ፍሬ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዱ​ር​ዋም ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ይበ​ላል።”


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በመ​ዐት እንደ ጐበ​ኘሁ፥ እን​ዲሁ በግ​ብፅ ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም እጐ​በ​ኛ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ጐበ​ዛ​ዝቷ በአ​ደ​ባ​ባ​ይዋ ላይ ይወ​ድ​ቃሉ፤ በዚ​ያም ቀን ሰል​ፈ​ኞች ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሕፃ​ና​ቱ​ንም በመ​ን​ገድ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቹ​ንም በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ቻ​ችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመ​ስ​ኮ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ሀገ​ራ​ችን ገብ​ቶ​አ​ልና።


ሣን። ብላ​ቴ​ና​ውና ሽማ​ግ​ሌው በመ​ን​ገ​ዶች ላይ ተጋ​ደሙ፤ ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ወድ​ቀ​ዋል፤ በረ​ኃብ ገደ​ል​ሃ​ቸው፤ በቍ​ጣ​ህም ቀን ሳት​ራራ አረ​ድ​ሃ​ቸው።


“በግ​ብፅ እንደ ሆነው ሞትን ሰደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ይፍ ገደ​ልሁ፤ ፈረ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ማ​ረ​ክሁ፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁም እሳ​ትን ሰድጄ አጠ​ፋ​ኋ​ችሁ፤ በዚ​ህም ሁሉ እና​ንተ ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች