ኤርምያስ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እኔም፥ “ወዮልኝ ጌታ እግዚአብሔር፥ እነሆ ሕፃን ነኝና እናገር ዘንድ አልችልም” አልሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት እንደምናገር አላውቅም፤ ገና ሕፃን ልጅ ነኝና” አልሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እኔም፦ “ወዮ! ጌታ አምላኬ፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና እንዴት እንደምናገር አላውቅም” አልሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ገና ልጅ ስለ ሆንኩ እንዴት እንደምናገር አላውቅም” ብዬ መለስኩለት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እኔም፦ ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና እናገር ዘንድ አላውቅም አልሁ። ምዕራፉን ተመልከት |