Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ያዕቆብ 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው ቢኖር የቤተ ክርስቲያን ካህናትን (ሽማግሌዎችን) ወደ እርሱ ይጥራ፤ እነርሱም በሽተኛውን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ያዕቆብ 5:14
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በብ​ላ​ቴ​ና​ውም ላይ ሦስት ጊዜ እፍ አለ​በት፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላ​ቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመ​ለስ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠራው።


ኤል​ሳ​ዕም ወደ ቤት ገብቶ በሩን በሁ​ለቱ ላይ ዘጋ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ።


ንዕ​ማን ግን ተቈ​ጥቶ ሄደ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ቆሞም የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ፥ የለ​ም​ጹ​ንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚ​ፈ​ው​ሰኝ መስ​ሎኝ ነበር።


እባቦችን ይይዛሉ፤የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይድናሉ።


ብዙ አጋንንትንም አወጡ፤ ብዙ ድውዮችንም ዘይት እየቀቡ ፈወሱአቸው።


እን​ደ​ዚ​ህም አድ​ር​ገው በበ​ር​ና​ባ​ስና በሳ​ውል እጅ ወደ ቀሳ​ው​ስት ላኩት።


ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ቀሳ​ው​ስ​ትን ሾሙ፤ ጾሙ፤ ጸለ​ዩም፤ ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አደራ ሰጡ​አ​ቸው።


ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሱ ጊዜም ምእ​መ​ና​ንና ሐዋ​ር​ያት፥ ቀሳ​ው​ስ​ትም ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ነገ​ሩ​አ​ቸው።


የፑ​ፕ​ል​ዮ​ስም አባት በን​ዳ​ድና በተ​ቅ​ማጥ ታሞ ተኝቶ ይኖር ነበር፤ ጳው​ሎ​ስም እርሱ ወዳ​ለ​በት ገብቶ ጸለ​የ​ለት፤ እጁ​ንም በላዩ ጭኖ ፈወ​ሰው።


ጴጥ​ሮ​ስም ሁሉን ካስ​ወጣ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ ጸለየ፤ ወደ በድ​ን​ዋም መለስ ብሎ፥ “ጣቢታ ሆይ፥ ተነሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም ዐይ​ኖ​ች​ዋን ገለ​ጠች፤ ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮ​ስን አየ​ችው፤ ቀና ብላም ተቀ​መ​ጠች።


ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች