Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 41:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ አለ​ቆች ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት ቀር​በው ፍር​ድን ይና​ገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ደሴቶች ሆይ፤ በፊቴ ዝም በሉ፤ አሕዛብ ኀይላቸውን ያድሱ! ቀርበው ይናገሩ፤ በፍርድም ፊት እንገናኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ደሴቶች ሆይ፥ በፊቴ ዝም በሉ፤ አሕዛብም ኃይላቸውን ያድሱ፤ ይቅረቡም በዚያን ጊዜም ይናገሩ፤ ለፍርድ በአንድነት እንቅረብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በደሴቶች የምትኖሩ ሕዝቦች! ጸጥ ብላችሁ አድምጡ! ሕዝቦች ኀይላቸውን ያድሱ፤ ወደ ፊትም ቀርበው ይናገሩ፤ በፍርድ ሸንጎ በአንድነት እንገናኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ደሴቶች ሆይ፥ በፊቴ ዝም በሉ፥ አሕዛብም ኃይላቸውን ያድሱ፥ ይቅረቡም በዚያን ጊዜም ይናገሩ፥ ለፍርድ በአንድነት እንቅረብ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 41:1
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ግ​ዲህ እንደ ሰው ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፥ አን​ተም መል​ስ​ልኝ።


“ኑና እን​ዋ​ቀስ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነ​ጻ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠ​ራ​ዋ​ለሁ።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከአ​ሦ​ርና ከግ​ብፅ፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኢ​ት​ዮ​ጵያ፥ ከኤ​ላ​ሜ​ጤን፥ ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ ለቀ​ሩት ለሕ​ዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እጁን ይገ​ል​ጣል።


እና​ንተ አሕ​ዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፤ እና​ን​ተም አለ​ቆች ሆይ፥ አድ​ምጡ፤ ምድ​ርና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ፥ ዓለ​ምና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ ሕዝብ ሁሉ ይስሙ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉና የሚ​ታ​ገሡ ግን ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወ​ጣሉ፤ ይሮ​ጣሉ፤ አይ​ታ​ክ​ቱ​ምም፤ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ራ​ቡ​ምም።


አሕ​ዛብ አይ​ተው ፈሩ። የም​ድ​ርም ዳር​ቾች ቀረቡ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ቀረቡ፤ መጡም።


አሳ​ስ​በኝ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሆነን እን​ፋ​ረድ፤ እን​ድ​ት​ጸ​ድቅ አስ​ቀ​ድ​መህ በደ​ል​ህን ተና​ገር።


አሕ​ዛብ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ፤ አለ​ቆ​ችም ተከ​ማቹ፤ ይህን ማን ይና​ገ​ራል? የቀ​ድ​ሞ​ው​ንስ ማን ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል? ይጸ​ድቁ ዘንድ ምስ​ክ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ያምጡ፤ ሰም​ተ​ውም፦ እው​ነ​ትን ይና​ገሩ።


ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህ​ንም ስሙ፤ እኔ ከጥ​ንት ጀምሬ በስ​ውር አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ከሆ​ነ​በት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበ​ርሁ፤ አሁ​ንም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና መን​ፈሱ ልከ​ው​ኛል።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ን​ተም አሕ​ዛብ፥ አድ​ምጡ፤ ከረ​ዥም ዘመን በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእ​ና​ቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠር​ቶ​አል፤


የሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእ​ኔስ ጋር የሚ​ከ​ራ​ከር ማን ነው? እስቲ በእኔ ላይ ይነሣ፤ የሚ​ከ​ራ​ከ​ረ​ኝስ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅ​ረብ።


እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፣ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።


እግዚአብሔር ከተቀደሰ ማደሪያው ነቅቶአልና ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሆይ፥ በፊቱ ዝም በል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች