Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አሁ​ንም አም​ነን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፥ አል​ፈ​ራም፥ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?” እን​በል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ በሙሉ ልብ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንላለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ስለዚህ በድፍረት፦ ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 13:6
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚ​ህም ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በራ​እይ ወደ አብ​ራም መጣ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አብ​ራም ሆይ፥ አት​ፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዋጋ​ህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤል​ያስ መጣ እን​ዲ​ህም አለው፦


ልባ​ቸው የቈ​ሰ​ለ​ውን ይፈ​ው​ሳል፥ ቍስ​ላ​ቸ​ው​ንም ያደ​ር​ቅ​ላ​ቸ​ዋል።


ሕዝ​ብ​ህን አድን፥ ርስ​ት​ህ​ንም ባርክ፥ ጠብ​ቃ​ቸው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ከፍ ከፍ አድ​ር​ጋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ይጠ​ብ​ቃል፥ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ አይ​ሰ​በ​ርም።


ልቤ በላዬ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ፥ የሞት ድን​ጋ​ጤም መጣ​ብኝ።


ነፍ​ሴን ከአ​ን​በ​ሶች መካ​ከል አዳ​ናት። ደን​ግ​ጬም ተኛሁ፤ የሰው ልጆች ጥር​ሳ​ቸው ጦርና ፍላጻ ነው፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም የተ​ሳለ ሾተል ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፍ ከፍ ይላል። መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው እንደ ልጆች ሕንፃ ሆነ፤


የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም አል​ዓ​ዛር ነበረ፤ “የአ​ባቴ አም​ላክ ረዳኝ፤ ከፈ​ር​ዖ​ንም እጅ አዳ​ነኝ” ብሎ​አ​ልና።


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቍ​ጥር ጥቂት የነ​በ​ርህ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እኔ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የሚ​ቤ​ዥ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው።


ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


እኛ ጸጋ​ንና ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ያገ​ኘ​ን​በት፥ በሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ​ሚ​ገ​ኘው ተስ​ፋም ያደ​ረ​ሰ​በት፤


እንደ ፍቁሩ አም​ላክ ማንም የለም፤ በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው፥ በጠ​ፈ​ርም በታ​ላ​ቅ​ነት ያለው እርሱ ረዳ​ትህ ነው።


እስ​ራ​ኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን​ነው? እርሱ ያጸ​ን​ሃል፤ ይረ​ዳ​ሃ​ልም፤ ትም​ክ​ሕ​ትህ በሰ​ይ​ፍህ ነው፤ ጠላ​ቶ​ችህ ውሸ​ታ​ሞች ናቸው፤ አን​ተም በአ​ን​ገ​ታ​ቸው ላይ ትጫ​ና​ለህ።”


እን​ግ​ዲህ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ደም ወደ መቅ​ደስ ለመ​ግ​ባት ባለ​ሙ​አ​ል​ነት አለን።


እን​ግ​ዲህ ምሕ​ረ​ትን እን​ድ​ን​ቀ​በል፥ በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንም ጊዜ የሚ​ረ​ዳ​ንን ጸጋ እን​ድ​ና​ገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእ​ም​ነት እን​ቅ​ረብ።


ለእ​ር​ሱም “የአ​ባቴ የሳ​ኦል እጅ አታ​ገ​ኝ​ህ​ምና አት​ፍራ፤ አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆ​ና​ለህ፤ እኔም ከአ​ንተ በታች እሆ​ና​ለሁ፤ ይህን ደግሞ አባቴ ሳኦል ያው​ቃል” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች