Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር በፍ​ቅር ኑሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እርስ በርሳችሁ እንደ ወንድማማች ተዋደዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እርስ በርሳችሁ መዋደዳችሁን ቀጥሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሁልጊዜ የእርስ በርስ የወንድማማችነት ፍቅር ይኑራችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1-2 የወንድማማች መዋደድ ይኑር። እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 13:1
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት አደ​ባ​ባ​ዮች የም​ት​ቆሙ እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ሁላ​ችሁ፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ።


እርስ በር​ሳ​ች​ሁም እን​ድ​ቷ​ደዱ ይህን አዝ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።


ኀም​ሳው ቀንም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት በአ​ንድ ቦታ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር።


ያመ​ኑ​ትም ሁሉ አንድ ልብና አን​ዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሁሉ ገን​ዘብ በአ​ን​ድ​ነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገን​ዘብ ነው” የሚል አል​ነ​በ​ረም።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ን​ተስ ለነ​ጻ​ነት ተጠ​ር​ታ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ ለነ​ጻ​ነ​ታ​ችሁ ምክ​ን​ያት አታ​ድ​ር​ጉ​ላት፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም በፍ​ቅር ተገዙ።


የመ​ን​ፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕ​ግ​ሥት፥ ምጽ​ዋት፥ ቸር​ነት፥ እም​ነት፥ ገር​ነት፥ ንጽ​ሕና ነው።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ በፍ​ቅር የም​ት​ሠራ እም​ነት እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ም​ምና፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ም​ምና።


በአ​ንድ መን​ፈ​ስና በሰ​ላም ማሰ​ሪ​ያ​ነት እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥


ክር​ስ​ቶስ እንደ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ራሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ የሚ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ቍር​ባን አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላ​ችሁ በፍ​ቅር ተመ​ላ​ለሱ።


ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፥ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤


በፍ​ቅ​ርና በበጎ ምግ​ባ​ርም ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችን ጋር እን​ፎ​ካ​ከር።


ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


ሁሉን አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፤ እንደወንድሞች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ፤


ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኀጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።


ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ፥ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ።


ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?


ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች