Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 49:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 የአ​ባ​ት​ህና የእ​ና​ትህ በረ​ከ​ቶች ጽኑ​ዓን ከሆኑ ከተ​ራ​ሮች በረ​ከ​ቶች ይልቅ ይበ​ል​ጣሉ፤ ዘለ​ዓ​ለ​ማ​ው​ያን ከሆኑ ከኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም በረ​ከ​ቶች ይልቅ ኀያ​ላን ናቸው፤ እነ​ር​ሱም በዮ​ሴፍ ራስ ላይ ይሆ​ናሉ፤ በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል አለቃ በሆ​ነ​ውም ራስ አናት ላይ ይሆ​ናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከጥንት ተራሮች በረከት፣ ከዘላለም ኰረብቶች ምርቃት ይልቅ፣ የአባትህ በረከት ይበልጣል። ይህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የአባትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፥ ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮረብቶችም በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፥ እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፥ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከጥንት ጀምሮ ጸንተው ከሚኖሩት ተራራዎችና ዘለዓለማውያን ከሆኑት ኮረብታዎችም ከሚገኘው ደስ ከሚያሰኝ በረከት ሁሉ የአባትህ በረከት ይበልጣል። እንግዲህ ይህ ሁሉ በረከት በዮሴፍ ራስ ላይ ይሁን፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም በዮሴፍ አናት ላይ ይውረድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የአባትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኅያላን ናቸው፤ ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮርፍቶች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 49:26
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ዴ​ዎ​ችም ሲያ​ልፉ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ ጐት​ተው አወ​ጡት፤ ለይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ዮሴ​ፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነ​ር​ሱም ዮሴ​ፍን ወደ ግብፅ ወሰ​ዱት።


ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ “በእኛ ላይ ልት​ነ​ግ​ሥ​ብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆ​ነን ይሆን?” አሉት። እን​ደ​ገ​ናም ስለ ሕል​ሙና ስለ ነገሩ የበ​ለጠ ጠሉት።


“ብን​ያም ነጣቂ ተኵላ ነው፤ በጥ​ዋት ይበ​ላል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንም ምግ​ቡን በማታ ለሕ​ዝብ ይሰ​ጣል።”


ተራ​ሮ​ችን እን​ዳ​ል​ቀ​ሥ​ፋ​ቸው እን​ዳ​ላ​ፈ​ል​ሳ​ቸ​ውም፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችም እን​ዳ​ይ​ነ​ዋ​ወጡ እንደ ማልሁ እን​ዲሁ ከእኔ ዘንድ ያለሽ ይቅ​ርታ አያ​ል​ቅም፤ የሰ​ላ​ምሽ ቃል ኪዳ​ንም አይ​ጠ​ፋም፤ መሓ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።


ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤ ጥልቁ ባሕር በዙ​ሪ​ያዬ ከበ​በኝ፤


ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን የተ​ለየ ያደ​ርግ ዘንድ ልዩ ስእ​ለት ቢሳል፥


“የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችም በዮ​ሴፍ ላይ ቀን​ተው ወደ ግብፅ ሀገር ሸጡት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።


በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ በመ​ን​ፈ​ሳዊ በረ​ከት ሁሉ የባ​ረ​ከን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች