Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 47:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እነ​ር​ሱም፥ “አንተ አዳ​ን​ኸን፤ በጌ​ታ​ች​ንም ፊት ሞገ​ስን አገ​ኘን፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሆ​ና​ለን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እነርሱም፣ “እንግዲህ ሕይወታችንን አትርፈህልናል፤ በጌታችን ፊት ሞገስ ካገኘን፣ ለፈርዖን ገባሮች እንሆናለን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እነርሱም፦ “አንተ ሕይወታችንን አተረፍክ፥ ጌታችንን ደስ የሚያሰኘው ከሆነ፥ ለፈርዖንም ባርያዎች እንሆናለን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሕዝቡም “ጌታችን ሆይ፥ ሕይወታችንን ስላዳንክልንና መልካም ነገር ስላደረግህልን ሁላችንም የፈርዖን ባሪያዎች እንሆናለን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እርሱም፦ አንተ አዳንኸን በጌታችን ፊት ሞገስን አናግኝ ለፈርዖንም ባሪያዎች እንሆናለን አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 47:25
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ በፊ​ት​ህስ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ ባሪ​ያ​ህን አት​ለ​ፈው፤


የላ​ካ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ያዕ​ቆብ ተመ​ል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ ሊቀ​በ​ልህ ይመ​ጣል፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”


ዔሳ​ውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉ ሰዎች ከፍዬ ልተ​ው​ል​ህን?” አለ። እር​ሱም፥ “ይህ ለም​ን​ድን ነው? በጌ​ታዬ ዘንድ ሞገ​ስን ማግ​ኘቴ ይበ​ቃ​ኛል” አለ።


ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ስም “እስ​ፍ​ን​ቶ​ፎ​ኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ የም​ት​ሆን አስ​ኔ​ት​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።


በመ​ከ​ርም ጊዜ ፍሬ​ውን ከአ​ም​ስት እጅ አን​ዱን እጅ ለፈ​ር​ዖን ስጡ፤ አራ​ቱም እጅ ለእ​ና​ንተ ለራ​ሳ​ችሁ፥ ለእ​ር​ሻው ዘርና ለእ​ና​ንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባ​ች​ሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”


ዮሴ​ፍም ለፈ​ር​ዖን ካል​ሆ​ነ​ችው ከካ​ህ​ናቱ ምድር በቀር አም​ስ​ተ​ኛው እጅ ለፈ​ር​ዖን እን​ዲ​ሆን በግ​ብፅ ምድር እስከ ዛሬ ሕግ አደ​ረ​ጋት።


እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።


ከእ​ን​ስሳ ሁሉ፥ ከተ​ን​ቀ​ሳ​ቃሽ አራ​ዊ​ትም ሁሉ፥ ሥጋ ካለው ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ትመ​ግ​ባ​ቸው ዘንድ ከሁ​ሉም ሁለት ሁለት ወደ መር​ከብ ታገ​ባ​ለህ፤ ተባ​ትና እን​ስት ይሁን።


እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኽኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ አለችው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች