Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 47:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዮሴ​ፍም ከግ​ብፅ ምድ​ርና ከከ​ነ​ዓን ምድር በእ​ህል ሸመታ የተ​ገ​ኘ​ውን ብሩን ሁሉ አከ​ማቸ፤ ዮሴ​ፍም ብሩን ወደ ፈር​ዖን ቤት አስ​ገ​ባው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዮሴፍ የግብጽና የከነዓን ሰዎች እህል በመሸመት የከፈሉትን ገንዘብ ሁሉ ሰብስቦ ወደ ፈርዖን ቤተ መንግሥት አስገባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ዮሴፍም የግብጽና የከነዓን ሕዝቦች የመጡ እህል ሲሸምቱ፥ ዮሴፍ ገንዘቡን ሰብስቦ ወደ ፈርዖን ግምጃ ቤት ያስገባው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ የግብጽና የከነዓን ሕዝቦች ወደ ዮሴፍ እየመጡ እህል ሲሸምቱ፥ ዮሴፍ ገንዘቡን ሰብስቦ ወደ ፈርዖን ግምጃ ቤት ያስገባው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ዮሴፍም ከግብፅ ምድርና ከከነዓን ምድር በእህል ሸመት የተገኘውን ብሩን ሁሉ አከማቸ ዮሴፍ ብሩን ወደ ፈርዖን ቤት አስገባው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 47:14
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ፤ ዮሴ​ፍም እህል ያለ​በ​ትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር።


ሀገ​ሮ​ችም ሁሉ ከዮ​ሴፍ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወጡ፤ በም​ድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበ​ርና።


ብሩም በግ​ብፅ ምድ​ርና በከ​ነ​ዓን ምድር አለቀ፤ የግ​ብፅ ሰዎ​ችም ሁሉ ወደ ዮሴፍ መጡ፤ እን​ዲህ ሲሉ፥ “በፊ​ትህ እን​ዳ​ን​ሞት እህል ስጠን፤ ብሩ አል​ቆ​ብ​ና​ልና።”


ስንዴውን የሚያደልብ ለአሕዛብ ይተወዋል። በረከት ግን በሚሰጥ ሰው ራስ ላይ ነው።


እን​ግ​ዲህ በዚህ ከመ​ጋ​ቢ​ዎች እያ​ን​ዳ​ንዱ ቸርና ታማኝ ሆኖ እን​ዲ​ገኝ ይፈ​ለ​ጋል።


ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች