Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 45:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዮሴ​ፍም ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ “እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕ​ይ​ወቱ ነውን?” አላ​ቸው። ወን​ድ​ሞ​ቹም ይመ​ል​ሱ​ለት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ ደን​ግ​ጠው ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ ለመሆኑ አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ?” ሲል ጠየቃቸው። ወንድሞቹ ግን በፊቱ ተደናግጠው ስለ ነበር መልስ ሊሰጡት አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዮሴፍም ለወንድሞቹ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፥ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ አለን?” አለ። ወንድሞቹም፥ በፊቱ ደንግጠው ነበርና፥ ሊመልሱለት አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዮሴፍ ወንድሞቹን “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕይወት አለን?” አላቸው። ወንድሞቹ የተናገረውን በሰሙ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፤ መልስ መስጠትም ተሳናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዮሴፍም ለወንድሞቹ፦ እኔ ዮሴፍ ነኝ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ ነውን? አለ። ወንድሞቹም ይመጠው ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 45:3
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኑ፥ እን​ግ​ደ​ለ​ውና በአ​ንድ ጕድ​ጓድ ውስጥ እን​ጣ​ለው፤ ክፉ አው​ሬም በላው እን​ላ​ለን፤ ሕል​ሞ​ቹም ምን እን​ደ​ሚ​ሆኑ እና​ያ​ለን።”


እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ተባ​ባሉ፥ “በእ​ው​ነት ወን​ድ​ማ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ እኛን በመ​ማ​ጠን ነፍሱ ስት​ጨ​ነቅ አይ​ተን አል​ሰ​ማ​ነ​ው​ምና፤ ስለ​ዚህ ይህ መከራ መጣ​ብን።”


ሮቤ​ልም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብላ​ቴ​ና​ውን አት​በ​ድሉ ብዬ​አ​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም፤ ስለ​ዚህ እነሆ፥ አሁን ደሙ ይፈ​ላ​ለ​ጋ​ች​ኋል።”


እር​ሱም ደኅ​ን​ነ​ታ​ቸ​ውን ጠየ​ቃ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የነ​ገ​ራ​ች​ሁኝ ሽማ​ግሌ አባ​ታ​ችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕ​ይ​ወት አለን?”


ስለ​ዚህ በፊቱ ደነ​ገ​ጥሁ፤ አስ​በ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም የተ​ነሣ እፈ​ራ​ለሁ።


አሁን ግን ሕማም በአ​ንተ ላይ መጥቶ ዳሰ​ሰህ። አን​ተም ተቸ​ገ​ርህ።


በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ሁሉ አይተውታልና ታወኩም። ወዲያውም ተናገራቸውና “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።


ወደ ግብ​ፅም እንደ ገና በተ​መ​ለሱ ጊዜ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ዐወ​ቁት፤ ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ዘመ​ዶች ዐወ​ቃ​ቸው።


ሳው​ልም፥ “አቤቱ፥ አንተ ማነህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ነኝ፤ በሾለ ብረት ላይ ብት​ቆም ለአ​ንተ ይብ​ስ​ሃል” አለው።


እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዐይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፤ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፤ አሜን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች