Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 45:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ለሁ​ሉም ሁለት ሁለት መለ​ወጫ ልብስ ሰጣ​ቸው፤ ለብ​ን​ያም ግን ሦስት መቶ ብርና አም​ስት መለ​ወጫ ልብስ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት የክት ልብስ ሰጣቸው፤ ለብንያም ግን ሦስት መቶ ጥሬ ብርና ዐምስት የክት ልብስ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ለእያንዳንዳቸውም አዳዲስ ልብስ ሰጣቸው፤ ለብንያም ግን አምስት የክት ልብስና ሦስት መቶ ብር ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ለእያንዳንዳቸውም አንድ አንድ የክት ልብስ ሰጣቸው፤ ለብንያም ግን አምስት የክት ልብስና ሦስት መቶ ብር ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ለመንገድ ስንቅ ሰጣቸው ለሁሉም ሁለት ሁለት መለወጫ ልብስ ሰጣቸው ለብንያም ግን ሦስት መቶ ብርና አምስት መለወጫ ልብስ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 45:22
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በፊ​ቱም ከአ​ለው መብል ፈን​ታ​ቸ​ውን አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የብ​ን​ያ​ምም ፈንታ ከሁሉ አም​ስት እጅ የሚ​በ​ልጥ ነበረ። እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ደስ አላ​ቸው።


ለአ​ባ​ቱም እን​ደ​ዚሁ ላከ፤ ከግ​ብፅ በረ​ከት ሁሉ የተ​ጫኑ ዐሥር አህ​ዮ​ችን፥ ደግ​ሞም በመ​ን​ገድ ለአ​ባቱ ስንቅ የተ​ጫኑ ዐሥር በቅ​ሎ​ዎ​ችን።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ ንዕ​ማ​ንን፥ “ሂድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ደብ​ዳቤ እል​ካ​ለሁ” አለው። እር​ሱም ሄደ፤ ዐሥ​ርም መክ​ሊት ብር፥ ስድ​ስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥ​ርም መለ​ወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።


ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።


ሶም​ሶ​ንም አላ​ቸው፥ “እን​ቆ​ቅ​ልሽ ልስ​ጣ​ችሁ፤ በሰ​ባ​ቱም በበ​ዓሉ ቀኖች ውስጥ ፈት​ታ​ችሁ ብት​ነ​ግ​ሩኝ፥ ሠላሳ የበ​ፍታ ቀሚ​ስና ሠላሳ ልውጥ ልብስ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስ​ቀ​ሎ​ናም ወረደ፤ ከዚ​ያም ሠላሳ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ገፍፎ እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን ለነ​ገ​ሩት ሰዎች ሰጠ። ሶም​ሶ​ንም ተቈጣ፤ ወደ አባ​ቱም ቤት ተመ​ለሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች