Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 45:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አን​ተም ወን​ድ​ሞ​ች​ህን፦ እን​ዲህ አድ​ርጉ በላ​ቸው፤ ከግ​ብፅ ምድር ለሕ​ፃ​ኖ​ቻ​ችሁ፥ ለሴ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሰረ​ገ​ሎ​ችን ውሰዱ፤ አባ​ታ​ች​ሁ​ንም ይዛ​ችሁ ኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “ደግሞም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፤ ‘ይህን አድርጉ፤ ከግብጽ ምድር ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን የምታጓጕዙበት ሠረገላዎች ወስዳችሁ፣ አባታችሁን ይዛችሁት ኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 አንተም ወንድሞችህን፦ እንዲህ አድርጉ በላቸው፥ ከግብጽ ምድር ለሕፃናቶቻችሁ ለሴቶቻችሁም ሰረገሎችን ውሰዱ፥ አባታችሁንም ይዛችሁ ኑ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እንዲሁም ሚስቶቻቸውን፥ ልጆቻቸውንና አባታቸውን አሳፍረው የሚያመጡበት ከግብጽ አገር ሠረገሎችን ይዘው እንዲሄዱ እዘዛቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 አንተም ወንድሞችህን፦ እንዲህ አድርጉ በላቸው ከግብፅ ምድር ለሕፃናቶቻችሁ ለሴቶቻችሁም ሰረገሎች ውሰዱ አባታችሁንም ይዛችሁ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 45:19
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለዕ​ቃ​ች​ሁም ዐይ​ና​ችሁ ለአ​የ​ውም ሁሉ አታ​ስቡ፤ የግ​ብፅ በረ​ከት ሁሉ ለእ​ና​ንተ ነውና።”


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም እንደ አዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ፤ ዮሴ​ፍም የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን እንደ ነገ​ረው ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ለመ​ን​ገድ ስን​ቅን ሰጣ​ቸው፤


እነ​ር​ሱም ዮሴፍ ያላ​ቸ​ውን፥ የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ው​ንም ነገር ሁሉ ነገ​ሩት፤ ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ዮሴፍ የላ​ካ​ቸ​ውን ሰረ​ገ​ሎች በአየ ጊዜ የአ​ባ​ታ​ቸው የያ​ዕ​ቆብ ልቡ፥ መን​ፈ​ሱም ታደሰ።


ያዕ​ቆ​ብም ከዐ​ዘ​ቅተ መሐላ ተነሣ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አባ​ታ​ቸ​ውን፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ውን፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም እነ​ር​ሱን ያመ​ጡ​ባ​ቸው ዘንድ ዮሴፍ በላ​ካ​ቸው ሰረ​ገ​ሎች ጭነው ወሰዱ።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ን​ተም አሕ​ዛብ፥ አድ​ምጡ፤ ከረ​ዥም ዘመን በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእ​ና​ቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠር​ቶ​አል፤


ነገ​ሥ​ታ​ትም አሳ​ዳ​ጊ​ዎች አባ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ እቴ​ጌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሞግ​ዚ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ግን​ባ​ራ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ አድ​ር​ገው ይሰ​ግ​ዱ​ል​ሻል፤ የእ​ግ​ር​ሽ​ንም ትቢያ ይል​ሳሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ እኔ​ንም በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ አያ​ፍ​ሩም።”


መባ​ቸ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ፤ የተ​ከ​ደኑ ስድ​ስት ሰረ​ገ​ሎች ዐሥራ ሁለ​ትም በሬ​ዎች፤ በየ​ሁ​ለ​ቱም አለ​ቆች አንድ ሰረ​ገላ አቀ​ረቡ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ በሬ በድ​ን​ኳኑ ፊት አቀ​ረቡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች