Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 41:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 ለዮ​ሴ​ፍም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይ​መጣ ተወ​ለ​ዱ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣቱ በፊት፣ የሄልዮቱ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደችለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣቱ በፊት፥ የሄልዮቱ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደችለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 ሰባቱ የራብ ዓመቶች ከመጀመራቸው በፊት፥ ዮሴፍ ከጶጢፌራ ልጅ ከአስናት ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ጶጢፌራ ኦን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ካህን ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 ለዮሴፍም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ አስናት የወለደችለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይመጣ ተወለዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 41:50
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ስም “እስ​ፍ​ን​ቶ​ፎ​ኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ የም​ት​ሆን አስ​ኔ​ት​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።


ዮሴ​ፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስን​ዴን አከ​ማቸ፤ መስ​ፈር እስ​ኪ​ሳ​ና​ቸው ድረስ፤ ሊሰ​ፈር አል​ተ​ቻ​ለ​ምና።


ዮሴ​ፍም የበ​ኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መከ​ራ​ዬን ሁሉ የአ​ባ​ቴ​ንም ቤት እን​ድ​ረሳ አደ​ረ​ገኝ፤”


ለዮ​ሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እነ​ር​ሱም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ናቸው። ሶር​ያ​ዊት ዕቅ​ብቱ የወ​ለ​ደ​ች​ለት የም​ና​ሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ የም​ና​ሴም ወን​ድም የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሱታ​ላና ጠኀን ናቸው። የሱ​ታላ ልጅም ኤዴን ነው።


አሁ​ንም እኔ ወደ አንተ ከመ​ም​ጣቴ በፊት በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ልህ ሁለቱ ልጆ​ችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍ​ሬ​ምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤ​ልና እንደ ስም​ዖን ናቸው።


የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያ​ስም አማ​ካሪ ነበረ፤ ከሊ​ታ​ው​ያ​ንና፥ ፊሊ​ታ​ው​ያን፥ የዳ​ዊ​ትም ልጆች የፍ​ርድ ቤት አለ​ቆች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች