Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 41:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ስም “እስ​ፍ​ን​ቶ​ፎ​ኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ የም​ት​ሆን አስ​ኔ​ት​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 ፈርዖንም ዮሴፍን ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱ ኦን ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ፈርዖንም ዮሴፍን “ጸፍናት ፐዕናህ” ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱጠ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ፈርዖን ለዮሴፍ “ጻፍናት ፐዕናሕ” የሚል መጠሪያ ስም አወጣለት፤ አስናት ተብላ የምትጠራውን የጶጢፌራን ልጅ በሚስትነት ሰጠው፤ ጶጢፌራ ኦን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ካህን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 ፈርዖንም የዮሴፍን ስም ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ጠራው የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ የምትሆን አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በግብፅ ምድር ሁሉ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 41:45
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሳ​ሌም ንጉሥ መልከ ጼዴ​ቅም እን​ጀ​ራ​ንና የወ​ይን ጠጅን አወጣ፤ እር​ሱም የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህን ነበረ።


ለዮ​ሴ​ፍም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይ​መጣ ተወ​ለ​ዱ​ለት።


ለዮ​ሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እነ​ር​ሱም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ናቸው። ሶር​ያ​ዊት ዕቅ​ብቱ የወ​ለ​ደ​ች​ለት የም​ና​ሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ የም​ና​ሴም ወን​ድም የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሱታ​ላና ጠኀን ናቸው። የሱ​ታላ ልጅም ኤዴን ነው።


የኢ​ያ​ዕር ሰው ኢራ​ስም ለዳ​ዊት ካህን ነበረ።


የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያ​ስም አማ​ካሪ ነበረ፤ ከሊ​ታ​ው​ያ​ንና፥ ፊሊ​ታ​ው​ያን፥ የዳ​ዊ​ትም ልጆች የፍ​ርድ ቤት አለ​ቆች ነበሩ።


ለም​ድ​ያ​ምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም የዮ​ቶ​ርን በጎች ይጠ​ብቁ ነበር፤ እነ​ር​ሱም መጥ​ተው ውኃ ቀዱ፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም የዮ​ቶ​ርን በጎች ሊያ​ጠጡ የው​ኃ​ዉን ገንዳ ሞሉ።


በግ​ብፅ ምድ​ርም ያለ​ውን የፀ​ሐይ ከተማ ምሰ​ሶ​ዎ​ችን ይሰ​ብ​ራል፥ የግ​ብ​ፅ​ንም አማ​ል​ክት ቤቶች በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላል።”


የሄ​ል​ዮቱ ከተ​ማና የቡ​ባ​ስ​ቱም ጐል​ማ​ሶች በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሴቶ​ችም ይማ​ረ​ካሉ።


በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ፤ ሰው ሁሉ ይቈ​ጠር ዘንድ ከአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ቄሣር ትእ​ዛዝ ወጣ።


ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አጋ​ቦስ የተ​ባለ አንድ ሰው ተነ​ሥቶ በዓ​ለም ሁሉ ጽኑ ረኃብ እን​ደ​ሚ​መጣ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ተገ​ል​ጦ​ለት ተና​ገረ፤ ይህም በቄ​ሣር ቀላ​ው​ዴ​ዎስ ዘመን ሆነ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች