Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 41:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ፈር​ዖን ቀለ​በ​ቱን ከእጁ አወ​ለቀ፤ በዮ​ሴ​ፍም እጅ አደ​ረ​ገው፤ የነጭ ሐር ልብ​ስ​ንም አለ​በ​ሰው፤ በአ​ን​ገ​ቱም የወ​ርቅ ዝር​ግ​ፍን አደ​ረ​ገ​ለት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ፈርዖን ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ በዮሴፍ እጅም አደረገው ነጭ የተልባ እግር ልብስንም አለበሰው በአንገቱም የወርቅ ዝርግፍን አደረገለት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 41:42
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም፥ “ምን መያዣ ልስ​ጥሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀለ​በ​ት​ህን፥ ኩፌ​ት​ህን፥ በእ​ጅህ ያለ​ውን በትር” አለች። እር​ሱም ሰጣ​ትና ከእ​ር​ስዋ ደረሰ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰ​ች​ለት።


የእ​ር​ሱም በም​ት​ሆን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ይቱ ሰረ​ገላ አስ​ቀ​መ​ጠው፤ ስገዱ እያ​ለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እን​ዲ​ሄድ አደ​ረገ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው።


እን​ዲሁ በመ​ጥ​ረ​ቢ​ያና በመ​ዶሻ ሰበ​ሩ​አት።


ለራስህ የክብር ዘውድን ለአንገትህም የወርቅ ድሪ ታገኛለህና።


ጕን​ጮ​ችሽ እንደ ዋኖስ እጅግ ያማሩ ናቸው፥ አን​ገ​ት​ሽም በዕ​ንቍ ድሪ ያማረ ነው።


እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ልቤን ማረ​ክ​ሽው፤ አንድ ጊዜ በዐ​ይ​ኖ​ችሽ፥ ከአ​ን​ገ​ት​ሽም ድሪ በአ​ንዱ፥ ልቤን ማረ​ክ​ሽው።


መስ​ተ​ዋ​ቱ​ንም ከጥሩ በፍታ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ልብስ፥ ራስ ማሰ​ሪ​ያ​ው​ንም፥ ዐይነ ርግ​ቡ​ንም ያስ​ወ​ግ​ዳል።


በወ​ህ​ኒም ውስጥ ለብ​ሶት የነ​በ​ረ​ውን ልብስ ለወ​ጠ​ለት፥ ኢኮ​ን​ያ​ንም በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ በፊቱ ሁል​ጊዜ እን​ጀራ ይበላ ነበር።


ዓላማ እን​ዲ​ሆ​ን​ልሽ ሸራሽ ከግ​ብፅ በፍ​ታና ከወ​ርቀ ዘቦ ተሠ​ር​ቶ​አል፤ መደ​ረ​ቢ​ያ​ሽም ከኤ​ሊሳ ደሴ​ቶች ሰማ​ያ​ዊና ቀይ ሐር ተሠ​ር​ቶ​አል።


አባ​ቱም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ‘ያማሩ ልብ​ሶ​ችን ቶሎ አም​ጡና አል​ብ​ሱት፤ ለጣ​ቱም ቀለ​በት፥ ለእ​ግ​ሩም ጫማ አድ​ር​ጉ​ለት፤’


ዮና​ታ​ንም የለ​በ​ሰ​ውን ካባ አው​ልቆ እር​ሱ​ንና ልብ​ሱን፥ ሰይ​ፉ​ንም፥ ቀስ​ቱ​ንም፥ ዝና​ሩ​ንም ለዳ​ዊት ሸለ​መው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች