Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 38:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ይሁ​ዳም፥ “እኛ መዘ​በቻ እን​ዳ​ን​ሆን ትው​ሰ​ደው፤ እነሆ፥ የፍ​የ​ሉን ጠቦት ላክ​ሁ​ላት፤ አን​ተም አላ​ገ​ኘ​ሃ​ትም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ይሁዳም፣ “እንግዲህ መያዣውን እንደ ያዘች ትቅር፣ አለዚያ መሣቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፤ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ይሁዳም፥ “እንግዲህ መያዣውን እንደ ያዘች ትቅር፤ አለዚያ መሣቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፤ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ይሁዳም “እንግዲህ ጠቦቱን ልኬላት ነበር፤ ነገር ግን ልታገኛት አልቻልክም፤ ስለዚህ ሰዎች መሳቂያ እንዳያደርጉን የወሰደችውን መያዣ እዚያው ታስቀረው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ይሁዳም፦ እኛ መዘበቻ እንዳንሆን ትውሰደው እነሆ የፍየሉን ጠቦት ሰደድሁላት አንተም አላገኘሃትም አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 38:23
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ይሁ​ዳም ተመ​ልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አላ​ገ​ኘ​ኋ​ትም፤ የሀ​ገሩ ሰዎች ደግሞ፦ ከዚህ ዘማ የለ​ችም” አሉኝ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከሦ​ስት ወር በኋላ ለይ​ሁዳ፥ “ምራ​ትህ ትዕ​ማር ሴሰ​ነች፤ እነሆ፥ በዝ​ሙት ፀነ​ሰች” ብለው ነገ​ሩት። ይሁ​ዳም፥ “አው​ጡ​አ​ትና በእ​ሳት ትቃ​ጠል” አለ።


አሁ​ንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነገር ለምን አቃ​ለ​ልህ? ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን በሰ​ይፍ መት​ተ​ሃል፤ ሚስ​ቱ​ንም ለአ​ንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስ​ደ​ሃል፤ እር​ሱ​ንም በአ​ሞን ልጆች ሰይፍ ገድ​ለ​ሃል።


ቍስልንና ውርደትን ያገኛል፥ ስድቡም ለዘለዓለም አይደመሰስም።


በዚ​ያን ጊዜ ሥራ​ች​ሁም እነሆ፥ ዛሬ ታፍ​ሩ​በ​ታ​ላ​ችሁ፤ መጨ​ረ​ሻው ሞት ነውና።


ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና።


በስ​ውር የሚ​ሠ​ሩት ሥራ ለመ​ና​ገር የሚ​ያ​ሳ​ፍር ነውና።


“እነሆ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ ኀፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች