Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 37:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አባ​ቱም ገሠ​ጸው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ይህ ያለ​ም​ኸው ሕልም ምን​ድን ነው? በውኑ እኔና እና​ትህ፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ህም መጥ​ተን በም​ድር ላይ እን​ሰ​ግ​ድ​ልህ ይሆን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሕልሙን ለአባቱና ለወንድሞቹ በነገራቸው ጊዜ፣ አባቱ “ይህ ያየኸው ሕልም ምንድን ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም በፊትህ ወደ ምድር ተጐንብሰን በርግጥ ልንሰግድልህ ነው?” ሲል ገሠጸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለአባቱና ለወንድሞቹም በነገራቸው ጊዜ፥ “ይህ ያለምኸው ሕልም ምንድነው? በውኑ እኔና እናትህ ወንድሞችህም መጥተን በምድር ላይ እንሰግድልህ ይሆን?” በማለት አባቱ ገሠጸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህንኑ ለወንድሞቹ የነገራቸውን ሕልም ለአባቱም በነገረው ጊዜ፥ አባቱ “ይህ ምን ዐይነት ሕልም ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም የምንሰግድልህ ይመስልሃልን?” በማለት ገሠጸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለአባቱና ለወንድሞቹም ነገራቸው አባቱም ገሠጸው እንዲህም አለው፦ ይህ ያለምኸው ሕልም ምንድር ነው? በውኑ እኔና እናትህ ወንድሞችህም መጥተን በምድር ላይ እንስገድልህ ይሆን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 37:10
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሕ​ዛብ ይገ​ዙ​ልህ፤ አለ​ቆ​ችም ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ጌታ ሁን፤ የአ​ባ​ት​ህም ልጆች ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ የሚ​ረ​ግ​ምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚ​ባ​ር​ክ​ህም ቡሩክ ይሁን።”


እነሆ፥ እኛ በእ​ርሻ መካ​ከል ነዶ ስና​ስር ነበ​ርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእ​ና​ን​ተም ነዶ​ዎች በዙ​ርያ ከብ​በው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”


ደግ​ሞም ሌላ ሕል​ምን አየ፤ ለአ​ባ​ቱና ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ነገ​ራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ደግሞ ሌላ ሕልም አለ​ምሁ፤ ሕል​ሙም እን​ዲህ ነው፦ ፀሐ​ይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋ​ክ​ብ​ትም ይሰ​ግ​ዱ​ልኝ ነበር።”


ዮሴ​ፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእ​ጃ​ቸው ያለ​ውን እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወድ​ቀው ሰገ​ዱ​ለት።


እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ባሪ​ያህ ሽማ​ግ​ሌው አባ​ታ​ችን ደኅና ነው፤ ገና በሕ​ይ​ወት አለ።” ዮሴ​ፍም አለ፥ “ሰው​የው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የባ​ረ​ከው ነው።” ራሳ​ቸ​ው​ንም ዝቅ አድ​ር​ገው ሰገ​ዱ​ለት።


ይሁ​ዳም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር ወደ ዮሴፍ ገባ፤ እር​ሱም ገና ከዚ​ያው ነበረ፤ በፊ​ቱም በም​ድር ላይ ወደቁ።


የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ሽም ልጆች እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ የና​ቁ​ሽም ሁሉ ወደ እግ​ርሽ ጫማ ይሰ​ግ​ዳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብ​ለ​ሽም ትጠ​ሪ​ያ​ለሽ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች