Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 33:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዔሳ​ውም፥ “ያገ​ኘ​ሁት ይህ ሠራ​ዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “በጌ​ታዬ ፊት ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ ነው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዔሳውም፣ “ወደ እኔ ተነድቶ የመጣው ይህ ሁሉ መንጋ ምንድን ነው?” አለው። እርሱም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ በአንተ ዘንድ ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እርሱም፥ “ያገኘሁት ይህ ሁሉ ጓዝ ምንህ ነው?” አለ። እርሱም፥ “በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ነው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዔሳውም “እፊት እፊትስ እየተነዳ ሲሄድ ያየሁት የእንስሶች መንጋ ምንድን ነው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እርሱ በአንተ ፊት ሞገስ እንዳገኝ የላክሁልህ ነው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እርሱም፦ ያገኘሁት ይህ ሠራዊት ሁሉ ምንህ ነው? አለ። እርሱም፦ በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ነው አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 33:8
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ላሞ​ች​ንም፥ ግመ​ሎ​ች​ንም፥ አህ​ዮ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም፥ ወን​ዶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ንም፥ ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ንም አገ​ኘሁ፤ አሁ​ንም በፊ​ትህ ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው ለመ​ን​ገር ላክሁ።”


የላ​ካ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ያዕ​ቆብ ተመ​ል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ ሊቀ​በ​ልህ ይመ​ጣል፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”


ደግ​ሞም ልያና ልጆ​ችዋ ቀር​በው ሰገ​ዱ​ለት፤ ከዚ​ያም በኋላ ዮሴ​ፍና ራሔል ቀር​በው ሰገዱ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በቤቱ ባለ​ውም ሁሉ ላይ ከሾ​መው በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ፃ​ዊ​ውን ቤት በዮ​ሴፍ ምክ​ን​ያት ባረ​ከው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በረ​ከት በቤ​ቱም፥ በእ​ር​ሻ​ውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች